Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 13:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሃ ግን ቍጣን አይቃወምም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የሰው ሀብቱ ለሕይወቱ ቤዛ ሊሆነው ይችላል፤ ድኻው ግን ሥጋት የለበትም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፥ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሀብታም በገንዘብ ሕይወቱን ለማዳን ይጣጣራል፤ ድኻ ግን የሚወሰድበት ሀብት ስለሌለው አይጨነቅም።

See the chapter Copy




ምሳሌ 13:8
15 Cross References  

ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


ሰይ​ጣ​ንም መልሶ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ቍር​በት ስለ ቍር​በት ነው፤ ሰው ያለ​ውን ሁሉ ስለ ሕይ​ወቱ ይሰ​ጣል።


በመካከልሽም የዋህና ትሑት ሕዝብን አስቀራለሁ፣ በእግዚአብሔርም ስም ይታመናሉ።


በዚ​ያም የተ​ገኙ ዐሥር ሰዎች ቀር​በው እስ​ማ​ኤ​ልን እን​ዲህ አሉት፥ “በሜ​ዳው ድልብ አለ​ንና፥ ገብ​ስና ስንዴ፥ ዘይ​ትና ማርም አለ​ንና አት​ግ​ደ​ለን፤” እር​ሱም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል እነ​ር​ሱን መግ​ደል ተወ።


የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ግን አን​ዳች ከሌ​ላ​ቸው ከሕ​ዝቡ ድሆች ከፊ​ሎ​ቹን በይ​ሁዳ ሀገር ተዋ​ቸው፤ የወ​ይ​ኑን ቦታና እር​ሻ​ው​ንም በዚያ ጊዜ ሰጣ​ቸው።


የጠብ ካሣ በምንም አይለወጥም፥ በገንዘብ ብዛትም አይታረቀውም።


የአ​በ​ዛ​ዎ​ችም አለቃ ከሀ​ገሩ ድሆች ወይን ተካ​ዮ​ችና አራ​ሾች እን​ዲ​ሆኑ አስ​ቀረ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም አጠ​ፋት፥ አለ​ቆ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ጽኑ​ዓ​ኑ​ንና ኀያ​ላ​ኑን ሁሉ፥ ጠራ​ቢ​ዎ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ቹ​ንም ሁሉ ዐሥር ሺህ ምር​ኮ​ኞ​ችን ሁሉ አፈ​ለሰ፤ ከሀ​ገሩ ድሆች በቀር ማንም አል​ቀ​ረም።


ከእ​ርሱ ግን ካሳ ቢፈ​ልጉ፥ የሕ​ይ​ወ​ቱን ካሳ የጫ​ኑ​በ​ትን ያህል ይስጥ።


ምንም ሳይኖራቸው ራሳቸውን ባለጠጎች የሚያደርጉ አሉ፥ ባለጠግነታቸው ብዙ ሲሆን ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉም አሉ።


ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤ የኃጥኣን መብራት ግን ትጠፋለች። የሐሰተኞች ነፍሳት በኀጢአት ይስታሉ። ጻድቃን ግን ይራራሉ፥ ይመጸውታሉም።


ዐዋቂ ሰው የጠቢባን ዘውድ ነው፤ የአላዋቂዎች ተግባር ግን ክፉ ነው።


ነፍስ ከም​ግብ ትበ​ል​ጣ​ለ​ችና፤ ሰው​ነ​ትም ከል​ብስ ይበ​ል​ጣ​ልና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements