Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 13:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ጻድቅ ሰውነቱ እስክትጠግብ ድረስ ይበላል፤ የኃጥኣን ሰውነት ግን ትቸገራለች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ጻድቅ እስኪጠግብ ድረስ ይበላል፤ የክፉዎች ሆድ ግን እንደ ተራበ ይኖራል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ጻድቅ ሰውነቱ እስክትጠግብ ድረስ ይበላል፥ የኀጥኣን ሆድ ግን ይራባል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እውነተኞች ሊበሉ የሚፈልጉትን ያኽል ያገኛሉ። ኃጢአተኞች ግን ዘወትር ይራባሉ።

See the chapter Copy




ምሳሌ 13:25
17 Cross References  

አጥ​ን​ቶች ሁሉ እን​ዲህ ይሉ​ሃል፦ “አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ድሃ​ውን ከሚ​ቀ​ማው እጅ ድሃ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ው​ንም ከሚ​ነ​ጥ​ቀው እጅ ታድ​ነ​ዋ​ለህ።”


እግዚአብሔር ጻድቅት ነፍስን አያስርብም፤ የኃጥኣንን ሕይወት ግን ከምድር ያስወግዳል።


ገን​ዘብ ሳት​ወዱ ኑሩ፤ ያላ​ች​ሁም ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ እርሱ “አል​ጥ​ል​ህም፤ ቸልም አል​ል​ህም” ብሎ​አ​ልና።


ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።


እንግዲህ ድህነት እንደ ክፉ መልእክተኛ፥ ችግርም እንደ ደኅና ርዋጭ ይመጣብሃል። ሰነፍ ባትሆን ግን ባለጸግነትህ እንደምንጭ ይመጣልሃል፤ ችግርም እንደ ክፉ ርዋጭ ከአንተ ይርቃል።


በራብ ያል​ቃሉ፤ ለሰ​ማይ ወፎ​ችም መብል ይሆ​ናሉ፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ይደ​ክ​ማል፥ ከም​ድር ይጠፉ ዘንድ የም​ድር አራ​ዊ​ትን ጥርስ፥ ከመ​ርዝ ጋር እል​ክ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን “ሊሠራ የማይወድ አይብላ፤” ብለን አዘናችሁ ነበርና።


ሁለትን ነገር ከአንተ እለምናለሁ፥ ሳልሞትም የሰጠኸኝን ጸጋህን አትከልክለኝ፤


የጠ​ላ​ቶቼ መዘ​ባ​በቻ አታ​ድ​ር​ገኝ ብያ​ለ​ሁና፥ እግ​ሬም ቢሰ​ና​ከል በእኔ ላይ ብዙ ነገ​ርን ይና​ገ​ራሉ።


ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤ ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።


በራ​ብና በጥ​ማት፥ በዕ​ራ​ቁ​ት​ነ​ትም፥ ሁሉ​ንም በማ​ጣት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ል​ክ​ብህ ለጠ​ላ​ቶ​ችህ ትገ​ዛ​ለህ፤ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ህም ድረስ በአ​ን​ገ​ትህ ላይ የብ​ረት ቀን​በር ይጭ​ናል።


ገን​ዘ​ቡ​ንም ሁሉ በጨ​ረሰ ጊዜ፥ በዚያ ሀገር ጽኑ ራብ መጣ፤ እር​ሱም ተቸ​ገረ።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ት​ና​ወጥ፥ ምድ​ርን መሠ​ረ​ታት፥ አጸ​ና​ትም።


ትምህርት ድህነትንና ጕስቍልናን ያስወግዳል፤ ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ይከብራል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements