Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 11:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የየራሳቸውን የሚዘሩና የሚያበዙ አሉ፤ እየሰበሰቡ የሚያጐድሉም አሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 አንዱ በለጋስነት ይሰጣል፤ ሆኖም ይበልጥ ያገኛል፤ ሌላው ያለ መጠን ይሰስታል፤ ግን ይደኸያል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በልግስና የሚሰጥ ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም፥ ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 አንዳንድ ሰዎች በለጋሥነት ገንዘባቸውን ይበትናሉ፤ ነገር ግን ሀብታቸው እየበዛ ይሄዳል፤ ሌሎች ደግሞ ያለ ልክ ለገንዘባቸው ይሳሳሉ፤ ነገር ግን ድኽነታቸው እየበዛ ይሄዳል።

See the chapter Copy




ምሳሌ 11:24
19 Cross References  

ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ እንደ ስጦታውም መልሶ ይከፍለዋል።


ስጡ፥ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልም፤ የሞ​ላና የበዛ፥ የተ​ት​ረ​ፈ​ረ​ፈም መል​ካም መስ​ፈ​ሪያ በዕ​ቅ​ፋ​ችሁ ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ በሰ​ፈ​ራ​ች​ሁ​በ​ትም መስ​ፈ​ሪያ ይሰ​ፍ​ሩ​ላ​ች​ኋል።”


እጅ​ህን በም​ት​ጥ​ል​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ዚህ በሥ​ራህ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃ​ልና ፈጽ​መህ ስጠው፤ የለ​መ​ነ​ህ​ንም ያህል አበ​ድ​ረው፤ በሰ​ጠ​ኸ​ውም ጊዜ በል​ብህ አት​ጸ​ጸት።


መካ​ኒ​ቱን በቤቱ የሚ​ያ​ኖ​ራት፥ ደስ የተ​ሰ​ኘ​ችም የል​ጆች እናት የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት።


ይህ ወይም ያ ማና​ቸው እን​ዲ​በ​ቅል ወይም ሁለቱ መል​ካም እንደ ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምና በማ​ለዳ ዘር​ህን ዝራ፥ በማ​ታም እጅ​ህን አት​ተው።


ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፣ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፣ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፣ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፣ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ።


ክፉ ሰው የበደልን ሥራ ይሠራል፤ ለጻድቃን ዘር ግን የታመነ ዋጋ አለው።


የጻድቃን ምኞት መልካም ነው፤ የኃጥኣን ተስፋ ግን ይጠፋል።


የተባረከች ሰውነት ሁሉ ትጠግባለች፥ ቍጡ ሰው ግን ክፉ ነው።


ምንም ሳይኖራቸው ራሳቸውን ባለጠጎች የሚያደርጉ አሉ፥ ባለጠግነታቸው ብዙ ሲሆን ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉም አሉ።


ከሳ​ዶ​ቅም ወገን የሆነ ታላቁ ካህን ዓዛ​ር​ያስ፥ “ሕዝቡ መባ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ማቅ​ረብ ከጀ​መረ ወዲህ በል​ተ​ናል፤ ጠጥ​ተ​ና​ልም፤ ጠግ​በ​ና​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን ባር​ኮ​አ​ልና ብዙ ተር​ፎ​አል፤ ከዚ​ህም ገና ብዙ ተረፈ” ብሎ ተና​ገረ።


ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements