Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 10:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ኃጥእ ከነገር ብዛት የተነሣ ከኀጢአት አያመልጥም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤ አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በቃል ብዛት ውስጥ መተላለፍ ሳይኖር አይቀርም፥ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከብዙ ንግግር ውስጥ ስሕተት አይጠፋም፤ ስለዚህ አስተዋይ ሰው ብዙ ከመናገር ይቈጠባል።

See the chapter Copy




ምሳሌ 10:19
13 Cross References  

ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤


ሕልም በብዙ መከራ፥ እን​ዲ​ሁም የሰ​ነፍ ቃል በብዙ ነገር ይመ​ጣ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በት​ዕ​ግ​ሥት ደጅ ጠና​ሁት፥ እር​ሱም ተመ​ልሶ ሰማኝ፥ የል​መ​ና​ዬ​ንም ቃል ሰማኝ።


“ብዙ እን​ደ​ም​ት​ና​ገር እን​ዲሁ መስ​ማት አለ​ብህ። ወይስ በን​ግ​ግ​ርህ ብዛት ጻድቅ የም​ት​ሆን ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን? ከሴ​ቶች የሚ​ወ​ለድ ዘመኑ ጥቂት የሆነ ቡሩክ ነው።


ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚያጸኑአትም ፍሬዋን ይበላሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ፥ አን​ተም በም​ድር ነህና በአ​ፍህ አት​ፍ​ጠን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቃልን ይና​ገር ዘንድ ልብህ አይ​ቸ​ኩል፤ ስለ​ዚ​ህም ቃልህ ጥቂት ይሁን።


ጥበብ የጐደለው የሀገሩን ሰው ይንቃል። ብልህ ሰው ግን ጸጥታን ያመጣል።


ሁለት ምላስ የሆነ ሰው የጉባኤን ምሥጢር ይገልጣል፤ በአንደበቱ የታመነ ግን ነገርን ይሰውራል።


ብልህ ሰው የጥበብ መንበር ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን መርገምን ያገኛል።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በም​ት​ሄ​ድ​በት ጊዜ እግ​ር​ህን ጠብቅ፤ የጠ​ቢ​ባ​ን​ንም ትም​ህ​ርት ለመ​ስ​ማት ቅረብ፤ ዳግ​መ​ኛም ከሰ​ነ​ፎች ስጦታ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ከመ​ቀ​በል ተጠ​በቅ፤ እነ​ርሱ መል​ካም ለመ​ሥ​ራት ዐዋ​ቂ​ዎች አይ​ደ​ሉ​ምና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements