Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ፊልጵስዩስ 2:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከእ​ርሱ በቀር፥ እንደ እኔ ሆኖ በማ​ስ​ተ​ዋል ግዳ​ጃ​ች​ሁን የሚ​ፈ​ጽም የለ​ኝ​ምና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለ እናንተ ደኅንነት ከልቡ የሚገድደው እንደ እርሱ ያለ ማንም የለኝም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እንደ እኔ ሆኖ ስለ ደኅንነታችሁ በቅንነት የሚጨነቅ እንደ እርሱ ያለ ማንም የለኝምና፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለ እናንተ ሁኔታ ከልብ የሚያስብ ከጢሞቴዎስ በቀር ሌላ ሰው የለኝም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እንደ እርሱ ያለ፥ ስለ ኑሮአችሁ በቅንነት የሚጨነቅ፥ ማንም የለኝምና፤

See the chapter Copy




ፊልጵስዩስ 2:20
16 Cross References  

እር​ሱን ብቻ ታስቡ ዘንድ፥ አንድ ልብና አንድ ምክ​ርም ሆና​ችሁ፥ በፍ​ቅር ትኖሩ ዘንድ ደስ​ታ​ዬን ፈጽ​ሙ​ልኝ።


ልጅ አባ​ቱን እን​ደ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግል፥ በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት እንደ አገ​ለ​ገ​ለኝ፥ የዚ​ህን ሰው ጠባ​ዩን ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም በመጣ ጊዜ በእ​ና​ንተ ዘንድ ያለ ፍር​ሀት እን​ዲ​ኖር ተጠ​ን​ቀቁ፤ እንደ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ይሠ​ራ​ልና።


ይህ​ንም ያለ፥ ድሆች አሳ​ዝ​ነ​ውት አይ​ደ​ለም፤ ሌባ ነበ​ርና፥ ሙዳየ ምጽ​ዋ​ቱ​ንም ሲጠ​ብቅ በው​ስጡ ከሚ​ገ​ባው ይወ​ስድ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ነው እንጂ።


ምን​ደ​ኛስ ይሸ​ሻል፤ ስለ በጎ​ችም አያ​ዝ​ንም፤ ምን​ደኛ ነውና።


ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ስለ ወደ​ደው ዮና​ታ​ንና ዳዊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።


በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ፤ ይህም እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፤ በአንተም ደግሞ እንዳለ ተረድቼአለሁ።


በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።


ኢዮ​ስ​ጦስ የተ​ባለ ኢያ​ሱም፥ ከግ​ዙ​ራን ሰዎች ወገን የሚ​ሆኑ እነ​ዚህ ሰላም ይሏ​ች​ኋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ሥራ ረዳ​ቶች እነ​ዚህ ብቻ ናቸው፤ እነ​ር​ሱም እኔን አጽ​ና​ን​ተ​ው​ኛል።


ነፍ​ሴን ከሞት፥ ዐይ​ኖ​ቼን ከዕ​ንባ፥ እግ​ሮቼ​ንም ከድጥ አድ​ነ​ሃ​ልና፥ በሕ​ያ​ዋን ሀገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው ዘንድ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ለሳ​ኦል መን​ገ​ሩን በፈ​ጸመ ጊዜ የዮ​ና​ታን ነፍስ በዳ​ዊት ነፍስ ታሰ​ረች፤ ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ወደ​ደው።


የት​ዕ​ግ​ሥ​ትና የመ​ጽ​ና​ናት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ፈቃድ እርስ በር​ሳ​ችን አንድ ዐሳብ መሆ​ንን ይስ​ጠን።


ስለዚህ ወንድሞችን ብታሳስብ፥ በእምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃል የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።


አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን አሳቤንም እምነቴንም ትዕግሥቴንም ፍቅሬንም መጽናቴንም


Follow us:

Advertisements


Advertisements