Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ፊልሞና 1:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አብረውኝም የሚሠሩ ማርቆስና አርስጥሮኮስ ዴማስም ሉቃስም ሰላምታ ያቀርቡልሃል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እንዲሁም ዐብረውኝ የሚሠሩት ማርቆስ፣ አርስጥሮኮስ፣ ዴማስና ሉቃስ ሰላምታ ያቀርቡልሃል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 አብረውኝም የሚሠሩ ማርቆስና አርስጥሮኮስ ዴማስም ሉቃስም ሰላምታ ያቀርቡልሃል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እንዲሁም የሥራ ጓደኞቼ የሆኑት ማርቆስ፥ አርስጥሮኮስ፥ ዴማስና፥ ሉቃስ ሰላምታ ያቀርቡልሃል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 አብረውኝም የሚሰሩ ማርቆስና አርስጥሮኮስ ዴማስም ሉቃስም ሰላምታ ያቀርቡልሃል።

See the chapter Copy




ፊልሞና 1:24
15 Cross References  

ወዳ​ጃ​ችን ባለ መድ​ኃ​ኒቱ ሉቃ​ስም ሰላም ብሎ​አ​ች​ኋል፤ ዴማ​ስም ሰላም ይላ​ች​ኋል።


ከእኔ ጋር የተ​ማ​ረ​ከው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮስ፥ ወደ እና​ንተ በሚ​መጣ ጊዜ ትቀ​በ​ሉት ዘንድ ስለ እርሱ ያዘ​ዝ​ኋ​ችሁ የበ​ር​ና​ባስ የአ​ባቱ ወን​ድም ልጅ ማር​ቆ​ስም፥


ከተ​ማ​ውም ሁሉ ታወከ፤ የመ​ቄ​ዶ​ን​ያን ሰዎች የጳ​ው​ሎ​ስን ወዳ​ጆች ጋይ​ዮ​ስ​ንና አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር እየ​ጐ​ተ​ቱ​በ​አ​ን​ድ​ነት ወደ ጨዋ​ታው ቦታ ሮጡ።


ከዚ​ህም በኋላ በአ​ስ​ተ​ዋለ ጊዜ ብዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች ተሰ​ብ​ስ​በው ይጸ​ል​ዩ​በት ወደ ነበ​ረው ማር​ቆስ ወደ​ተ​ባ​ለው ወደ ዮሐ​ንስ እናት ወደ ማር​ያም ቤት ሄደ።


በተ​ነ​ሣ​ንም ጊዜ ወደ እስያ በም​ት​ሄድ በአ​ድ​ራ​ማ​ጢስ መር​ከብ ተሳ​ፈ​ርን፤ የተ​ሰ​ሎ​ንቄ ሀገር ሰው የሚ​ሆን መቄ​ዶ​ን​ያ​ዊው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስም አብ​ሮን ሄደ።


በር​ና​ባ​ስና ሳው​ልም አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውን ፈጽ​መው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስ​ንም አስ​ከ​ት​ለ​ውት መጡ።


እንግዲህ ከእውነት ጋር አብረን እንድንሠራ እኛ እንዲህ ያሉትን በእንግድነት ልንቀበል ይገባናል።


ወን​ድ​ሜና አጋዤ ስት​ሪካ ሆይ፥ እን​ድ​ት​ረ​ዳ​ቸው አን​ተ​ንም እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ወን​ጌ​ልን በማ​ስ​ተ​ማር ከቀ​ሌ​ም​ን​ጦ​ስና ሥራ​ቸው ከተ​ባ​በረ፥ ስማ​ቸ​ውም በሕ​ይ​ወት መጽ​ሐፍ ከተ​ጻ​ፈ​ላ​ቸው ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ሁሉ ጋር ከእ​ኔም ጋር ደክ​መ​ዋ​ልና።


አሁ​ንም አብ​ሮኝ የሚ​ሠ​ራ​ውን ወን​ድ​ማ​ች​ንን አፍ​ሮ​ዲ​ጡን ወደ እና​ንተ ልል​ከው አስ​ቤ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም የክ​ር​ስ​ቶስ ሎሌ ነው፤ ለእ​ና​ን​ተም መም​ህ​ራ​ችሁ ነው፤ ለእ​ኔም ለች​ግሬ ጊዜ መል​እ​ክ​ተ​ኛዬ ነው።


ቲቶም ቢሆን፥ ስለ እና​ንተ አብ​ሮኝ የሚ​ሠራ ጓደ​ኛዬ ነው፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ቢሆኑ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር የአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሐዋ​ር​ያት ናቸው።


ከዚ​ህም በኋላ እነ ጳው​ሎስ ከጳፉ ከተማ ወጥ​ተው ሄዱና የጵ​ን​ፍ​ልያ አው​ራጃ ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ጰር​ጌን ገቡ፤ ዮሐ​ንስ ግን ትቶ​አ​ቸው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሰ።


ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን፥ ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements