Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ ያድ​ር​ጉት፤ ከቂጣ እን​ጀ​ራና ከመ​ራራ ቅጠል ጋር ይብ​ሉት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ይህንም በሁለተኛው ወር፣ በዐሥራ አራተኛው ቀን ፀሓይ በምትጠልቅበት ጊዜ ያክብሩ፤ የፋሲካውንም በግ፣ ከቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋራ ይብሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በዓሉንም በሁለተኛው ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ ያክብሩ፤ እርሾ ካልገባበት ቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ዘግይተው ሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት እንዲያከብሩ ተፈቅዶላቸዋል፤ ሲያከብሩም እርሾ የሌለበትን ቂጣ ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በሁለተኛው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ ያድርጉት፤ ከቂጣ እንጀራና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት።

See the chapter Copy




ዘኍል 9:11
7 Cross References  

ይህ ሁሉ የሆ​ነው “ከእ​ርሱ ዐፅ​ሙን አት​ስ​በሩ” ያለው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።


የቦ​ካ​ውን እን​ጀራ ከእ​ርሱ ጋር አት​ብላ፤ ከግ​ብፅ ሀገር በች​ኮላ ስለ ወጣህ ከግ​ብፅ ሀገር የወ​ጣ​ህ​በ​ትን ቀን በዕ​ድ​ሜህ ሁሉ ታስብ ዘንድ የመ​ከ​ራን እን​ጀራ፥ ቂጣ እን​ጀራ ሰባት ቀን ከእ​ርሱ ጋር ብላ።


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊ​ዜው አድ​ር​ጉት፤ እንደ ሥር​ዐቱ ሁሉ እንደ ፍር​ዱም ሁሉ አድ​ር​ጉት።”


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ና​ንተ ወይም ከት​ው​ል​ዶ​ቻ​ችሁ ዘንድ ማን​ኛ​ውም ሰው በሰ​ው​ነቱ ቢረ​ክስ፥ ወይም ሩቅ መን​ገድ ቢሄድ፥ ወይም በተ​ወ​ለ​ዳ​ች​ሁ​በት ሀገር ያለም ቢሆን እርሱ ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲ​ካን ያድ​ርግ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements