ዘኍል 8:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ታነጻቸው ዘንድ እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ በማንጻት ውኃ ትረጫቸዋለህ፤ ሰውነታቸውን ሁሉ ይላጩ፤ ልብሳቸውንም ይጠቡ፤ ንጹሓንም ይሆናሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ስታነጻቸውም እንዲህ አድርግ፤ በሚያነጻ ውሃ እርጫቸው፤ ገላቸውን በሙሉ በምላጭ ተላጭተው ልብሳቸውን ይጠቡ፤ በዚህም ይንጹ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እነርሱንም ለማንጻት እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ ኃጢአትን የሚያነጻውን ውኃ እርጫቸው፥ በገላቸውም ላይ ያለውን ጠጉር ሁሉ በምላጭ ይላጩ፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፥ ራሳቸውንም ንጹሕ ያድርጉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ለመንጻት ሥርዓት በተዘጋጀው ውሃ እርጫቸው፤ በሰውነታቸው ላይ ያለውን ጠጒር ሁሉ እንዲላጩና ልብሳቸውንም አጥበው ራሳቸውን እንዲያነጹ አድርግ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ታነጻቸው ዘንድ እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ ኃጢአትን የሚያነጻውን ውኃ እርጫቸው፥ በገላቸውም ሁሉ ምላጭ ያሳልፉ፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፥ ይታጠቡም። See the chapter |