Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የመ​ቅ​ረ​ዝ​ዋም ሥራዋ እን​ዲህ ነበረ። ሁለ​ን​ተ​ና​ቸው ወርቅ የሆነ አፅ​ቆ​ችዋ ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ አበ​ቦ​ች​ዋም ሁለ​ን​ተ​ና​ቸው ሥረ-ወጥ ነበሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ሳ​የው ምሳሌ መቅ​ረ​ዝ​ዋን እን​ዲሁ አደ​ረገ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የመቅረዙ አሠራር እንዲህ ነበር፤ ከመቆሚያው እስከ አበቦቹ ያለው ከተቀጠቀጠ ወርቅ የተሠራ ሲሆን፣ የመቅረዙም አሠራር እግዚአብሔር ለሙሴ ባሳየው መሠረት ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 መቅረዙም እንዲህ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ተሠራ፤ ከእግሩ እስከ አበቦቹ ድረስ ሥራው ተቀጥቅጦ የተሠራ ነበረ፤ ጌታ ሙሴን እንዳሳየው ምሳሌ መቅረዙን እንዲሁ አድርጎ ሠራው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 መቅረዙም እግዚአብሔር ለሙሴ ባሳየው ዕቅድ መሠረት እስከ አገዳውና አበባው ድረስ ከተቀጠቀጠ ወርቅ የተሠራ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 መቅረዙም እንዲህ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ተሠራ፤ እስከ አገዳውና እስከ አበቦቹ ድረስ ከተቀጠቀጠ ሥራ ነበረ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳሳየው ምሳሌ መቅረዙን እንዲሁ አደረገ።

See the chapter Copy




ዘኍል 8:4
11 Cross References  

ሁለት ኪሩ​ቤል ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ወርቅ ሥራ፤ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ በሁ​ለት ወገን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።


በተ​ራ​ራው እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ሁሉ፥ እንደ ማደ​ሪ​ያው ምሳሌ፥ እንደ ዕቃ​ውም ሁሉ ምሳሌ ለእኔ ትሠ​ራ​ለህ፤ እን​ዲሁ ትሠ​ራ​ለህ።


በሰ​ማይ ባለው አም​ሳል የተ​ሠ​ራው ይህ ሥራ፥ በዚህ ደም የሚ​ነጻ ከሆነ፥ ይህ ሰማ​ያዊ መሥ​ዋ​ዕ​ትስ ከዚህ ይበ​ል​ጣል።


እነ​ር​ሱም ሙሴ ድን​ኳ​ኒ​ቱን ሲሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰ​ማ​ያዊ ነገር ምሳ​ሌና ጥላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያገ​ለ​ግ​ላሉ፤ “በተ​ራ​ራው እንደ ተገ​ለ​ጠ​ልህ ምሳሌ ሁሉን ታደ​ርግ ዘንድ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎት ነበ​ርና።


ሁለት ኪሩ​ቤ​ል​ንም ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ወርቅ ሠራ፤ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ በሁ​ለት ወገን አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ድን​ኳ​ኑ​ንም በተ​ራ​ራው ላይ በአ​ሳ​የ​ሁህ ምሳሌ ሥራ።


አሮ​ንም እን​ዲሁ አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ በመ​ቅ​ረዙ ፊት መብ​ራ​ቶ​ቹን አበራ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


Follow us:

Advertisements


Advertisements