Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በግ​ብፅ ምድር ያለ​ውን በኵር ሁሉ በገ​ደ​ል​ሁ​በት ቀን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በኵ​ራት ሁሉ፥ ሰው ወይም እን​ስሳ፥ ለእኔ ቀድ​ሼ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና የእኔ ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከሰውም ሆነ ከእንስሳ በእስራኤል የተወለደ ማንኛውም በኵር ተባዕት የእኔ ነው፤ በግብጽ የነበረውን በኵር ሁሉ በመታሁ ጊዜ የእኔ እንዲሆኑ ለይቻቸዋለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በግብጽ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በገደልሁበት ቀን የእስራኤልን ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ሰው ወይም እንስሳ፥ ለእኔ ቀድሼአቸዋለሁና የእኔ ናቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በግብጽ ምድር በኲር ሆኖ የተወለደውን በገደልኩ ጊዜ ከእያንዳንዱ እስራኤላዊ ቤተሰብ በኲር ሆኖ የተወለደውንና የእንስሶችንም በኲር ሁሉ ለእኔ የተለየ እንዲሆን ቀድሼው ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ በገደልሁበት ቀን የእስራኤልን ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ሰው ወይም እንስሳ፥ ለእኔ ቀድሼአቸዋለሁና የእኔ ናቸው።

See the chapter Copy




ዘኍል 8:17
18 Cross References  

“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ከሰ​ውም፥ ከእ​ን​ስ​ሳም መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይ​ልኝ፤ የእኔ ነው።”


“በኵር ሆኖ የሚ​ወ​ለድ ወንድ ልጅ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይባ​ላል” ተብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ እንደ ተጻፈ፥


ለፍጥረቱ የበኵራት ዐይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።


ቸነ​ፈር በኵ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ባ​ቸው በእ​ም​ነት ፋሲ​ካን አደ​ረገ፤ ደሙ​ንም ረጨ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ የከዳ፥ ያን​ንም የተ​ቀ​ደ​ሰ​በ​ትን የኪ​ዳ​ኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቈ​ጠረ፥ የጸ​ጋ​ው​ንም መን​ፈስ ያክ​ፋፋ እን​ዴት ይልቅ የሚ​ብስ ቅጣት የሚ​ገ​ባው ይመ​ስ​ላ​ች​ኋል?


እነ​ር​ሱም በእ​ው​ነት ቅዱ​ሳን ይሆኑ ዘንድ ስለ እነ​ርሱ እኔ ራሴን እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።


እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነኝ ብላ​ችሁ፥ አብ የቀ​ደ​ሰ​ው​ንና ወደ ዓለ​ምም የላ​ከ​ውን እን​ዴት ትሳ​ደ​ባ​ለህ? ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ።


የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸ​ውም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእ​ኔና በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ምል​ክት ይሆኑ ዘንድ ሰን​በ​ታ​ቴን ሰጠ​ኋ​ቸው።


ለፀ​ሐይ ቀንን ያስ​ገ​ዛው፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ተገዙ፥ በደ​ልም ሆነ​ባ​ቸው።


በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና፤ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ርን ሁሉ በመ​ታሁ ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ በኵ​ርን ሁሉ፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን፥ ለእኔ ለይ​ች​አ​ለሁ፤ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”


“ከእ​ን​ስ​ሳህ የሚ​ወ​ለድ በኵር ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ማንም ይለ​ው​ጠው ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም እቀ​ድ​ሳ​ለሁ፤ በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋን ከተ​ቀ​መ​ጠው ከፈ​ር​ዖን በኵር ጀምሮ እስከ ውኃ ቀጅዋ ምር​ኮኛ በኵር ድረስ፥ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ሩን ሁሉ፥ የእ​ን​ስ​ሳ​ው​ንም በኵር ሁሉ መታ።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ ሌዋ​ው​ያ​ንን ወስ​ጄ​አ​ለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements