Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 8:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እነ​ር​ሱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵ​ራት ሁሉ፥ መጀ​መ​ሪያ በሚ​ወ​ለድ ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስ​ጄ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እነርሱም ሙሉ በሙሉ የእኔ እንዲሆኑ የተሰጡኝ እስራኤላውያን ናቸው፤ ከማንኛዪቱም እስራኤላዊት በተወለደ በኵር ወንድ ልጅ ምትክ የራሴ እንዲሆኑ ወስጃቸዋለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እነርሱም ከእስራኤል ልጆች መካከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰጥተዋልና፤ በእስራኤል ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ማኅፀን በሚከፍተው ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስጄአቸዋለሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኔ እነርሱን በኲር ሆነው ለሚወለዱት ለእስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ሁሉ ምትክ አድርጌ ስለ መረጥኳቸው የእኔ ብቻ ይሆናሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እነርሱም ከእስራኤል ልጆች መካከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰጥተዋልና፤ በእስራኤል ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ማኅፀን በሚከፍት ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስጄአቸዋለሁ።

See the chapter Copy




ዘኍል 8:16
6 Cross References  

“እነሆ፥ እኔ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ መጀ​መ​ሪያ በሚ​ወ​ለ​ደው በበ​ኵር ሁሉ ፋንታ ሌዋ​ው​ያ​ንን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይች ወስ​ጃ​ለሁ፤ በእ​ነ​ርሱ ፋንታ ሌዋ​ው​ያን ለእኔ ይሁኑ፤


“ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌ​ዋ​ው​ያ​ን​ንም እን​ስ​ሶች በእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው ፋንታ ውሰድ፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም ለእኔ ይሁኑ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።


ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ አሮ​ንና ወደ ልጆቹ ወደ ካህ​ናቱ ታገ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ። ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተለ​ይ​ተው ለእኔ ሀብት ሆነው ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና።


“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ከሰ​ውም፥ ከእ​ን​ስ​ሳም መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይ​ልኝ፤ የእኔ ነው።”


“የሌ​ዊን ነገድ አቅ​ር​በህ ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ በካ​ህኑ በአ​ሮን ፊት አቁ​ማ​ቸው።


በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና፤ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ርን ሁሉ በመ​ታሁ ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ በኵ​ርን ሁሉ፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን፥ ለእኔ ለይ​ች​አ​ለሁ፤ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements