Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 መባ​ቸ​ው​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረቡ፤ የተ​ከ​ደኑ ስድ​ስት ሰረ​ገ​ሎች ዐሥራ ሁለ​ትም በሬ​ዎች፤ በየ​ሁ​ለ​ቱም አለ​ቆች አንድ ሰረ​ገላ አቀ​ረቡ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ በሬ በድ​ን​ኳኑ ፊት አቀ​ረቡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስድስት የተሸፈኑ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት በሬዎች ይኸውም ከእያንዳንዱ አለቃ አንዳንድ በሬ እንዲሁም ከየሁለቱ አለቆች አንድ ሠረገላ ስጦታ አድርገው ወደ እግዚአብሔር ፊት አመጡ፤ እነዚህንም በማደሪያው ድንኳን ፊት አቀረቧቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 መባቸውንም በጌታ ፊት አመጡ፥ የተሸፈኑ ስድስት ሰረገሎች ዐሥራ ሁለትም በሬዎች፤ ለሁለትም አለቆች ለእያንዳንዳቸው አንድ ሠረገላ ለእያንዳንዱም አለቃ አንዳንድ በሬ አመጡ፤ በማደሪያው ፊት አቀረቡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 መባቸውን ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤ ያቀረቡአቸውም መባዎች በየሁለቱ አለቆች ስም አንድ ሠረገላ፥ እንዲሁም በእያንዳንዱ አለቃ ስም አንድ በሬ ሆኖ፥ ስድስት ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት በሬዎች ነበሩ፤ እነዚህንም መባዎች በመገናኛው ድንኳን ፊት አቀረቡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 መባቸውንም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ፥ የተከደኑ ስድስት ሰረገሎች አሥራ ሁለትም በሬዎች፤ በየሁለቱም አለቆች አንድ ሰረገላ አቀረቡ፥ ሁሉም እያንዳንዱ አንድ በሬ በማደሪያው ፊት አቀረቡ።

See the chapter Copy




ዘኍል 7:3
7 Cross References  

አን​ተም ወን​ድ​ሞ​ች​ህን፦ እን​ዲህ አድ​ርጉ በላ​ቸው፤ ከግ​ብፅ ምድር ለሕ​ፃ​ኖ​ቻ​ችሁ፥ ለሴ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሰረ​ገ​ሎ​ችን ውሰዱ፤ አባ​ታ​ች​ሁ​ንም ይዛ​ችሁ ኑ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን በም​ስ​ጋና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እን​ደ​ሚ​ያ​መጡ፥ እን​ዲሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ይሆን ዘንድ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ሁሉ፥ በፈ​ረ​ሶ​ችና በሰ​ረ​ገ​ሎች፥ በአ​ል​ጋ​ዎ​ችና በበ​ቅ​ሎ​ዎች፥ በጠ​ያር ግመ​ሎ​ችም ላይ አድ​ር​ገው፥ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ወደ ተቀ​ደ​ሰ​ችው ከተማ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ስለ​ዚህ ሠረ​ገላ ብር​ዑን እን​ዲ​ያ​ደቅ፥ በበ​ታ​ቻ​ችሁ ባለ መሬት እኔ አደ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም እንደ አዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ፤ ዮሴ​ፍም የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን እንደ ነገ​ረው ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ለመ​ን​ገድ ስን​ቅን ሰጣ​ቸው፤


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በል​ባ​ችሁ ያሰ​ባ​ች​ሁ​ትን ከገ​ን​ዘ​ባ​ችሁ መባ አም​ጡ​ልኝ” በላ​ቸው።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች አያ​ሌ​ዎች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በስ​ፍ​ራው ይሠ​ሩት ዘንድ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ሰጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements