Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 6:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ካህ​ኑም የተ​ቀ​ቀ​ለ​ውን የአ​ው​ራ​ውን በግ ወርች፥ ከሌ​ማ​ቱም አንድ ቂጣ እን​ጎቻ፥ አን​ድም ስስ ቂጣ ይወ​ስ​ዳል፤ የተ​ሳ​ለ​ው​ንም የራስ ጠጕር ከተ​ላጨ በኋላ በባ​ለ​ስ​እ​ለቱ እጆች ላይ ያኖ​ራ​ቸ​ዋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “ ‘ናዝራዊው ተስሎ የተለየበትን ጠጕር ከተላጨ በኋላ፣ ካህኑ የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች እንዲሁም ከመሶቡ ላይ እርሾ የሌለበትን አንድ ወፍራምና አንድ ስስ ቂጣ ወስዶ ናዝራዊው ያስይዘው

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ካህኑም የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች፥ ከሌማቱም እርሾ ያልገባበትን አንድ የቂጣ እንጐቻ እርሾም ያልገባበትን አንድ ስስ ቂጣ ይወስዳል፥ የተቀደሰውንም የራስ ጠጉር ከተላጨ በኋላ በናዝራዊው እጆች ላይ ያኖራቸዋል፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “ናዝራዊው የተቀደሰውን ጠጒሩን ከተላጨ በኋላ ካህኑ የተቀቀለውን አውራ በግ ወርች፥ በመሶብ ውስጥ ካለው አንድ ኅብስትና አንድ ስስ ቂጣ ወስዶ ናዝራዊ በሆነው ሰው እጆች ላይ ያኖረዋል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ካህኑም የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች፥ ከሌማቱም አንድ ቂጣ እንጐቻ አንድም ስስ ቂጣ ይወስዳል፥ የተለየውንም የራስ ጠጕር ከተላጨ በኋላ በናዝራዊው እጆች ላይ ያኖራቸዋል፤

See the chapter Copy




ዘኍል 6:19
7 Cross References  

ደግ​ሞም ስቡ ሳይ​ጤስ የካ​ህኑ ልጅ መጥቶ የሚ​ሠ​ዋ​ውን ሰው፥ “ጥሬ​ውን እንጂ የተ​ቀ​ቀ​ለ​ውን ሥጋ ከአ​ንተ አይ​ወ​ስ​ድ​ምና እጠ​ብ​ስ​ለት ዘንድ ለካ​ህኑ ሥጋ ስጠኝ” ይለው ነበር።


የእ​ርሱ እጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳ​ቱን ቍር​ባን ያመ​ጣሉ፤ ፍር​ም​ባ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቍር​ባን ያቀ​ርብ ዘንድ በጉ​በቱ ላይ ያለ​ውን መረ​ብና የፍ​ር​ም​ባ​ውን ስብ ያመ​ጣል።


ሙሴም አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን አላ​ቸው፥ “ሥጋ​ውን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በተ​ቀ​ደ​ሰው ቦታ ቀቅሉ፤ አሮ​ንና ልጆቹ ይብ​ሉት ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘኝ በዚያ እር​ሱ​ንና በቅ​ድ​ስ​ናው መሶብ ያለ​ውን እን​ጀራ ብሉ።


ሁሉ​ንም በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ እጆች ላይ አደ​ረገ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቍር​ባ​ንን አቀ​ረበ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን የተ​ለየ ያደ​ርግ ዘንድ ልዩ ስእ​ለት ቢሳል፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements