ዘኍል 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 በላዩም የአቆስጣውን ቍርበት መሸፈኛ ያድርጉበት፤ ከእርሱም በላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ያግቡበት፤ መሎጊያዎቹንም ያግቡበት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ከዚያም በአቆስጣው ቍርበት ይሸፍኑት፤ ሙሉ በሙሉ ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ በላዩ ላይ ይዘርጉበት፤ መሎጊያዎቹንም በየቦታው ያስገቡ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 በእርሱም ላይ የአስቆጣውን ቁርበት መሸፈኛ ያድርጉበት፥ ከእርሱም በላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 የተለፋውንም የቊርበት መሸፈኛ በመጋረጃው ላይ አድርገው በዚያም ላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ዘርግተው ያልብሱት፤ መሎጊያዎችንም ያስገቡ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 በላዩም የአስቆጣውን ቁርበት መሸፈኛ ያድርጉበት፥ ከእርሱም በላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። See the chapter |
የሚያገለግሉበትን ዕቃውን ሁሉ፥ ማንደጃዎቹን፥ ሜንጦዎቹንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ መክደኛዎቹንም፥ ያመድ ማፍሰሻዎቹን፥ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ ያስቀምጡበት፤ በእርሱም የአቆስጣን ቍርበት መሸፈኛ ይዘርጉ፤ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። ሐምራዊዉንም መጐናጸፊያ ወስደው ማስታጠቢያውንና ማስቀመጫውን ይሸፍኑት፤ በአቆስጣው ቍርበት መሸፈኛ ውስጥም አድርገው በመሸከሚያዎቹ ላይ ያኑሩት፤