ዘኍል 4:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)45 እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው የሜራሪ ልጆች ወገኖች ቍጥር ይህ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም45 ይህ የሜራሪ ጐሣዎች ጠቅላላ ድምር ነው፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሙሴና አሮን እነዚህን ቈጠሯቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)45 ጌታ በሙሴ አንደበት እንዳዘዘ፥ ከሜራሪ ልጆች ወገኖች የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም45 እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉትና ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው የሜራሪ ልጆች እነዚህ ናቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)45 እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ፥ ከሜራሪ ልጆች ወገኖች የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው። See the chapter |