Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 4:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ባለው ሥራ​ቸው ሁሉ የሜ​ራሪ ልጆች ወገ​ኖች አገ​ል​ግ​ሎት ይህ ነው፤ እነ​ር​ሱም ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ይሆ​ናሉ።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እንግዲህ የሜራሪያውያን ጐሣዎች በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር ሥር ሆነው በመገናኛው ድንኳን ሲሠሩ አገልግሎታቸው ይህ ነው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር ቁጥጥር ሥር ሆነው በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ባለው አገልግሎታቸው ሁሉ የሜራሪ ልጆች ወገኖች አገልግሎት ይህ ነው።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር ተቈጣጣሪነት የሚካሄደው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሜራሪ ልጆች ቤተሰብ አገልግሎት ይህ ነው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 የሜራሪ ልጆች ወገኖች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከኢታምር እጅ በታች በየአገልግሎታቸው ሁሉ ይህ ነው።

See the chapter Copy




ዘኍል 4:33
7 Cross References  

የጌ​ድ​ሶን ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ይህ ነው፤ ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ይሆ​ናሉ።


ሰውም በአ​ባቱ ቤተ ሰብእ ውስጥ ወን​ድ​ሙን ይዞ፥ “አንተ ልብስ አለህ፥ አለ​ቃም ሁን​ልን፥ ምግ​ባ​ች​ንም ከእ​ጅህ በታች ትሁን” ቢለው፥


ኢያ​ሱም ካህ​ና​ቱን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​ማ​ችሁ በሕ​ዝቡ ፊት ሂዱ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​መው በሕ​ዝቡ ፊት ሄዱ።


በዙ​ሪ​ያ​ውም የሚ​ቆ​ሙት የአ​ደ​ባ​ባዩ ምሰ​ሶ​ዎች፥ እግ​ሮ​ቹም፥ የአ​ደ​ባ​ባዩ ደጃፍ መጋ​ረጃ ምሰ​ሶ​ዎች፥ እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካስ​ማ​ዎ​ቹም፥ አው​ታ​ሮ​ቹም፥ ዕቃ​ዎ​ቹና ማገ​ል​ገ​ያ​ዎቹ ሸክ​ማ​ቸው ነው፤ የሚ​ጠ​ብ​ቁ​ት​ንም የሸ​ክ​ማ​ቸ​ውን ዕቃ ሁሉ በየ​ስ​ማ​ቸው ቍጠሩ።


ሙሴና አሮ​ንም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አለ​ቆች የቀ​ዓ​ትን ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።


በካ​ህኑ በአ​ሮን ልጅ በይ​ታ​ምር እጅ የሌ​ዋ​ው​ያን ተል​እኮ ይሆን ዘንድ ሙሴ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ደ​ታ​ዘዘ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥር​ዐት ይህ ነው።


ከካ​ህ​ኑም ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ላሉት ለሜ​ራሪ ልጆች እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው መጠን አራት ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ስም​ንት በሬ​ዎ​ችን ሰጣ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements