Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 36:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ ያዘ​ዛ​ቸው ትእ​ዛዝ፥ ሥር​ዐ​ትና ፍርድ እነ​ዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከኢያሪኮ ማዶ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ፣ በሞዓብ ሜዳ ሳሉ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ትእዛዞችና ደንቦች እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ጌታ በሙሴ አንደበት የእስራኤልን ልጆች በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ሜዳ ያዘዛቸው ትእዛዝና ፍርድ እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለእስራኤላውያን በኢያሪኮ ትይዩ ከዮርዳኖስ ወንዝ ባሻገር ባለው በሞአብ ሜዳ ላይ በነበሩበት ጊዜ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጣቸው ትእዛዞችና ሥርዓቶች እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እግዚአብሔር በሙሴ እጅ የእስራኤልን ልጆች በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ሜዳ ያዘዛቸው ትእዛዝና ፍርድ እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy




ዘኍል 36:13
12 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ዘንድ ሙሴን ያዘ​ዘው ትእ​ዛ​ዛት እነ​ዚህ ናቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጓዙ፤ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በሞ​ዓብ ምዕ​ራ​ብም ሰፈሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው።


ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት በሞ​ዓብ ሜዳ ላይ እን​ዲህ ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ር​ሱና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ የሰ​ጣ​ቸው ሥር​ዐ​ቶ​ችና ፍር​ዶች፥ ሕግ​ጋ​ትም እነ​ዚህ ናቸው።


“በበግ ጠጕር ልብስ፥ ወይም በተ​ልባ እግር ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተ​ደ​ረገ ነገር ላይ ቢሆን፥ ንጹሕ ወይም ርኩስ ያሰኝ ዘንድ የለ​ምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።”


“የእ​ን​ስ​ሳና የወፍ፥ በው​ኃ​ውም ውስጥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የፍ​ጥ​ረት ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የፍ​ጥ​ረት ሁሉ ሕግ ይህ ነው።


ከዮ​ሴፍ ልጅ ከም​ናሴ ልጆች ወገ​ኖች ባሎ​ቻ​ቸ​ውን አገቡ፥ ርስ​ታ​ቸ​ውም በአ​ባ​ታ​ቸው ነገድ ጸና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements