Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 35:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ነፍሰ ገዳዩ በማ​ኅ​በሩ ፊት ለፍ​ርድ እስ​ከ​ሚ​ቆም ድረስ እን​ዳ​ይ​ሞት፥ ከተ​ሞቹ ከደም ተበ​ቃይ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እነዚህም፣ ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ዘንድ ለፍርድ ከመቅረቡ በፊት እንዳይሞት ከደም ተበቃዩ የሚሸሽባቸው የመማፀኛ ከተሞች ይሆናሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹ ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በዚያም የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ከሚፈልግ ከሟቹ ዘመድ ሊሰወር ይችላል፤ በግድያ ወንጀል የተከሰሰ ሰው ለፍርድ ሳይቀርብ መገደል የለበትም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹም ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ።

See the chapter Copy




ዘኍል 35:12
10 Cross References  

ባለ ደሙ ነፍሰ ገዳ​ዩን በልቡ ተና​ድዶ እን​ዳ​ያ​ሳ​ድ​ደው መን​ገ​ዱም ሩቅ ስለ​ሆነ አግ​ኝቶ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው፥ አስ​ቀ​ድሞ ጠላቱ አል​ነ​በ​ረ​ምና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም።


በማ​ኅ​በሩ ፊት እስ​ኪ​ቆ​ምና እስ​ኪ​መ​ረ​መር ድረስ ባለ​ደሙ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው ሳያ​ውቅ ሰውን የገ​ደለ ወደ​ዚያ እን​ዲ​ማ​ፀን፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ በመ​ካ​ካ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ቀ​መጥ መጻ​ተኛ የተ​መ​ረጡ ከተ​ሞች እነ​ዚህ ናቸው።


እነ​ሆም፥ ዘመ​ዶች ሁሉ በባ​ሪ​ያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደ​ለው ስለ ወን​ድሙ ነፍስ እን​ገ​ድ​ለው ዘንድ ወን​ድ​ሙን የገ​ደ​ለ​ውን አውጪ አሉኝ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ይ​ቀር ወራ​ሹን የቀ​ረ​ውን መብ​ራ​ቴን ያጠ​ፋሉ፤”


ደም ተበ​ቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳ​ዩን ይግ​ደል፤ ባገ​ኘው ጊዜ ይግ​ደ​ለው።


የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም ስድ​ስቱ ከተ​ሞች የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።


“የነ​ፍሰ ገዳይ ሕግ ይህ ነው፤ ቀድሞ ጠላቱ ሳይ​ሆን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ሳያ​ውቅ የገ​ደለ ወደ​ዚያ ሸሽቶ በሕ​ይ​ወት ይኑር።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ በሙሴ ቃል የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞ​ችን ስጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements