Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 33:55 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

55 የሀ​ገ​ሩ​ንም ስዎች ከፊ​ታ​ችሁ ባታ​ሳ​ድዱ፥ ያስ​ቀ​ራ​ች​ኋ​ቸው ለዐ​ይ​ና​ችሁ እንደ እሾህ፥ ለጐ​ና​ች​ሁም እንደ አሜ​ከላ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል፤ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ምድር ያስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ኋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

55 “ ‘የምድሪቱን ነዋሪዎች አሳድዳችሁ ሳታስወጧቸው ብትቀሩ ግን፣ እንዲኖሩ የተዋችኋቸው ሰዎች ለዐይናችሁ ስንጥር፣ ለጐናችሁም እሾኽ ይሆኑባችኋል፤ በምትኖሩበትም ምድር ችግር ይፈጥሩባችኋል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

55 የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ ስንጥር ለጎናችሁም እንደ እሾህ ይሆኑባችኋል፥ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

55 በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ አሳዳችሁ ካላጠፋችሁ ግን ያስቀራችኋቸው ለዐይናችሁ እንደ ስንጥር ለጐናችሁም እንደ እሾኽ በመሆን ያስቸግሩአችኋል፤ በምትቀመጡባትም ምድር ዘወትር ጦርነት በማስነሣት ያስጨንቁአችኋል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

55 የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ እሾህ ለጎናችሁም እንደሚወጋ ነገር ይሆኑባችኋል፥ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል።

See the chapter Copy




ዘኍል 33:55
11 Cross References  

ስለ​ዚ​ህም እኔ አሕ​ዛ​ብን ከፊ​ታ​ችሁ አላ​ወ​ጣ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ያስ​ጨ​ን​ቋ​ች​ኋል፤ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወጥ​መድ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል” አልሁ።


አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የአ​ሕ​ዛብ ምርኮ ትበ​ላ​ለህ፤ ዐይ​ን​ህም አታ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ ያም ለአ​ንተ ክፉ ይሆ​ን​ብ​ሃ​ልና አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አታ​ም​ል​ካ​ቸው።


ልጅ​ህን ከእኔ ያር​ቀ​ዋ​ልና፤ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትም ያመ​ል​ካ​ልና። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ ይነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋል፤ ፈጥ​ኖም ያጠ​ፋ​ች​ኋል።


እኔን እን​ድ​ት​በ​ድል እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጉህ በሀ​ገ​ርህ ላይ አይ​ቀ​መጡ፤ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ብታ​መ​ልክ ወጥ​መድ ይሆ​ኑ​ብ​ሃ​ልና።”


ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት የሚ​ወጋ እሾህ፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ከአሉ ከና​ቋ​ቸው ሁሉ የሚ​ያ​ቈ​ስል ኩር​ን​ችት አይ​ሆ​ንም፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


ስለ​ዚ​ህም ቢሆን በብዙ ራእይ እን​ዳ​ል​ታ​በይ ሰው​ነ​ቴን የሚ​ወጋ እር​ሱም የሚ​ጐ​ስ​መኝ የሰ​ይ​ጣን መል​እ​ክ​ተኛ ተሰ​ጠኝ።


እኔም በእ​ነ​ርሱ አደ​ር​ገው ዘንድ ያሰ​ብ​ሁ​ትን በእ​ና​ንተ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።”


በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ወደ ቀሩት ወደ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ አት​ግቡ፤ የአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ስሞች በእ​ና​ንተ መካ​ከል አይ​ጠሩ፤ አት​ማ​ሉ​ባ​ቸ​ውም፤ አታ​ም​ል​ኳ​ቸ​ውም፤ አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements