Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 33:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ካህ​ኑም አሮን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአ​ር​ባ​ኛው ዓመት፥ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር፥ ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ሞተ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 በእግዚአብሔር ትእዛዝ ካህኑ አሮን ወደ ሖር ተራራ ወጣ፤ እዚያም እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በአርባኛው ዓመት፣ በዐምስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ካህኑም አሮን በጌታ ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ካህኑ አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።

See the chapter Copy




ዘኍል 33:38
5 Cross References  

“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የማ​ስቢ ወገን ከሚ​ሆን ከኢ​ያ​ቅም ልጆች ቦታ ከቤ​ሮስ ተጓዙ። በዚ​ያም አሮን ሞተ፤ ተቀ​በ​ረም፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ አል​ዓ​ዛር ካህን ሆነ።


ወን​ድ​ምህ አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ፥ ወደ ወገ​ኖ​ቹም እንደ ተጨ​መረ፥ በወ​ጣ​ህ​በት ተራራ ሙት፤ ወደ ወገ​ኖ​ች​ህም ተጨ​መር፤


አሮ​ንም በሖር ተራራ ላይ በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበረ።


በአ​ር​ባ​ኛው ዓመት በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን፥ ሙሴ እን​ዲ​ነ​ግ​ራ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ነገ​ራ​ቸው፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements