Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 31:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለ​ዩ​ትን ግብር ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ሰጠው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው የእግዚአብሔር ድርሻ የሆነውን ግብር ለካህኑ አልዓዛር ሰጠው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ ለጌታ የስጦታ ቁርባን የሆነውን ግብር ለካህኑ ለአልዓዛር ሰጠው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ስለዚህም ሙሴ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት መባውን ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ በማድረግ ለአልዓዛር ሰጠው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ ለእግዚአብሔር ለማንሣት ቍርባን የሆነውን ግብር ለካህኑ ለአልዓዛር ሰጠው።

See the chapter Copy




ዘኍል 31:41
14 Cross References  

የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ዩ​ትን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን መባ ሁሉ ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም ጋር ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ችህ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ይህም ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም በኋላ ለዘ​ርህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግና የሁ​ል​ጊዜ ቃል ኪዳን ነው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእኔ የለ​ዩ​ትን የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ቍር​ባ​ኔን ሁሉ ትጠ​ብቁ ዘንድ ለአ​ንተ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ለአ​ንተ እስ​ክ​ታ​ረጅ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።


ይህ​ንም ነገር ንኡሰ ክር​ስ​ቲ​ያን ይስ​ማው፤ መል​ካ​ሙ​ንም ነገር ሁሉ ከሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረው ይማር።


ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​አ​ቸው የተ​ቀ​ደሱ ነገ​ሮች ሁሉ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ለካ​ህኑ ነው።


የተ​ቀ​ደሰ የሰው ነገር ሁሉ፥ ሰውም ለካ​ህኑ የሚ​ሰ​ጠው ሁሉ ለእ​ርሱ ይሁን።”


ሰዎ​ቹም ዐሥራ ስድ​ስት ሺህ ነበሩ ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብር ሠላሳ ሁለት ነበረ።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እኩ​ሌ​ታም፥ ወደ ሰልፍ ከወ​ጡት ወን​ዶች ላይ ሙሴ የለ​የው፥


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሄዱ፤ እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements