Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 3:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የጌ​ድ​ሶን ልጆች በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ጠ​ብ​ቁት ማደ​ሪ​ያ​ውና ድን​ኳኑ፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ውም፥ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 የጌርሶናውያን ኀላፊነት በመገናኛው ድንኳን ማደሪያውንና ድንኳኑን፣ መደረቢያዎቹን እንዲሁም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ያለውን መጋረጃ፣

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ጌድሶናውያንም በመገናኛው ድንኳን የሚጠብቁት ማደሪያውን፥ ድንኳኑን፥ መደረቢያውን፥ የመገናኛውንም ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በመገናኛው ድንኳን የጌርሾን ልጆች ኀላፊነት የነበረው በመገናኛው ድንኳን፥ ከውጪና ከውስጥ በኩል ባለው መሸፈኛ፥ በመግቢያው ደጃፍ መጋረጃ፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ጌድሶናውያንም በመገናኛው ድንኳን የሚጠብቁት ማደሪያው፥ ድንኳኑም፥ መደረቢያውም፥ የመገናኛው ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥

See the chapter Copy




ዘኍል 3:25
23 Cross References  

በተ​ራ​ራው እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ሁሉ፥ እንደ ማደ​ሪ​ያው ምሳሌ፥ እንደ ዕቃ​ውም ሁሉ ምሳሌ ለእኔ ትሠ​ራ​ለህ፤ እን​ዲሁ ትሠ​ራ​ለህ።


ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! አስቀድሞ ስለ አንተ እንደ ተነገረው ትንቢት፥ በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ፤


አክ​ር​ጳ​ንም “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሾ​ም​ህ​ባ​ትን መል​እ​ክ​ት​ህን እን​ድ​ት​ፈ​ጽ​ማት ተጠ​ን​ቀቅ” በሉት።


ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነው፤ ለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም የካ​ህ​ና​ት​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ንን ሰሞን በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸ​ውና በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ በሮች የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡና ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ፥ ያመ​ሰ​ግ​ኑም፥ ያከ​ብ​ሩም ዘንድ ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን መደበ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥር​ዐት፥ የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን የአ​ሮ​ንን ልጆች ሥር​ዐት ለመ​ጠ​በቅ ሹሞ​አ​ቸው ነበር።


ድን​ኳ​ኑም ተነ​ቀለ፤ ድን​ኳ​ኑ​ንም የተ​ሸ​ከሙ የጌ​ድ​ሶን ልጆ​ችና የሜ​ራሪ ልጆች ተጓዙ።


ለጌ​ድ​ሶን ልጆች እንደ አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሁለት ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና አራት በሬ​ዎ​ችን ሰጣ​ቸው።


የድ​ን​ኳ​ኑን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሕጉ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሕግ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ይጠ​ብቁ።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዘው በድ​ን​ኳኑ ደጅ ፊት መጋ​ረ​ጃ​ውን ዘረጋ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው መጋ​ረ​ጃ​ውን በድ​ን​ኳኑ ላይ ዘረ​ጋው፤ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም መደ​ረ​ቢያ በላዩ አደ​ረ​ገ​በት።


ነገር ግን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በዕ​ቃ​ዎ​ችዋ ሁሉ፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ባለው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋ​ው​ያ​ንን አቁ​ማ​ቸው። ድን​ኳ​ን​ዋ​ንና ዕቃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ ይሸ​ከሙ፤ ያገ​ል​ግ​ሉ​አ​ትም፤ በድ​ን​ኳ​ን​ዋም ዙሪያ ይስ​ፈሩ።


የጌ​ድ​ሶን አባ​ቶች ቤት አለቃ የዳ​ሔል ልጅ ኤሊ​ሳፍ ይሆ​ናል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements