Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “የሌ​ዊን ልጆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውም ቍጠር፤ ወን​ዱን ሁሉ ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ቍጠ​ራ​ቸው።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “ሌዋውያንን በየቤታቸውና በየጐሣቸው ቍጠር፤ የምትቈጥረውም አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ ነው” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 “የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገናቸውም ቁጠር፤ ወንዱን ሁሉ ዕድሜው አንድ ወር የሞላውንና ከዚያም በላይ ያለውን ቁጠራቸው።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “ሌዋውያንን በየወገናቸውና በየቤተሰባቸው መድበህ ቊጠር፤ ከተወለደ አንድ ወር የሞላውንና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ ቊጠር።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገናቸውም ቍጠር፤ ወንዱን ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ቍጠራቸው።

See the chapter Copy




ዘኍል 3:15
17 Cross References  

ከአ​ንድ ወርም ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ ወን​ዶች ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠሩ ሃያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል ርስት አል​ተ​ሰ​ጣ​ቸ​ው​ምና ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም።


ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን አውቀሃል።


ኢየሱስ ግን አይቶ ተቈጣና “ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ፤ አትከልክሉአቸው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሩቅ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “በዘ​ለ​ዓ​ለም ፍቅር ወድ​ጄ​ሃ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ በቸ​ር​ነት ሳብ​ሁህ።


“ሂድ፤ እን​ዲህ ብለህ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጆሮ ተና​ገር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ት​ሽን ምሕ​ረት፥ የታ​ጨ​ሽ​በ​ት​ንም ፍቅር፥ በም​ድረ በዳ ዘር ባል​ተ​ዘ​ራ​በት ምድር እንደ ተከ​ተ​ል​ሽኝ አስ​ቤ​አ​ለሁ።


እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ እኔንም የሚሹ ሞገስን ያገኛሉ።


ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠሩ ወን​ዶች በኵ​ሮች ሁሉ በየ​ስ​ማ​ቸው ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ሃያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ነበሩ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ወን​ዶች ሁሉ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ስድ​ስት ሽህ አምሳ ነበሩ።


ወን​ዶች ሁሉ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ስም​ንት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ፤ መቅ​ደ​ሱ​ንም ይጠ​ብቁ ነበር።


ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠ​ሩት የወ​ን​ዶች ሁሉ ቍጥር ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።


ሌዋ​ው​ያን ግን በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ነገድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም።


ሙሴና አሮ​ንም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዛ​ቸው ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።


ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡ​ትን ሁሉ፥ አን​ተና አሮን በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ቍጠ​ሩ​አ​ቸው።


የሌዊ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የተ​ቈ​ጠ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ ከጌ​ድ​ሶን የጌ​ድ​ሶ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከቀ​ዓት የቀ​ዓ​ታ​ው​ያን ወገን፥ ከሜ​ራሪ የሜ​ራ​ራ​ው​ያን ወገን።


በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤት ለተ​ቈ​ጠሩ ካህ​ናት፥ ከሃያ ዓመ​ትም ወደ ላይ ላሉ በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸ​ውና በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ለተ​ቈ​ጠሩ ሌዋ​ው​ያን፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements