Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 29:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ከላ​ሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት፥ የበግ ጠቦ​ቶች፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እንከን የሌለባቸውን አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ምንም ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች፥ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥

See the chapter Copy




ዘኍል 29:2
9 Cross References  

ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ፥ ከላ​ሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውም ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከላ​ሞች ሁለት በሬ​ዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥


በእ​ሳ​ትም የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከላ​ሞች ሁለት በሬ​ዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።


“በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወሩ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ቀን ለእ​ና​ንተ ይህች ዕለት የተ​ቀ​ደ​ሰች ናት፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት፤ ምል​ክት ያለ​ባት ቀን ትሁ​ን​ላ​ችሁ።


ለእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸው በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለበ​ሬው ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአ​ው​ራው በግ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥


“መባ​ውም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን ያቀ​ር​ባል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት እን​ዲ​ኖ​ረው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ማቅ​ረብ ጀመሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ግን ገና አል​ተ​መ​ሠ​ረ​ተም ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements