Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 29:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ የሚ​ቀ​ርቡ ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን ከመጠጡም ቁርባን ሌላ ለኃጢአት መሥዋዕት ደግሞ አንድ አውራ ፍየል አቅርቡ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስለ ኃጢአት ስርየትም የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል ታቀርባላችሁ፤ ይህንንም ሁሉ መሥዋዕት የምታቀርቡት በየቀኑ ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት የእህል ቊርባንና የመጠጥ መባ ጋር ተጨማሪ በማድረግ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ የሚቀርቡ ናቸው።

See the chapter Copy




ዘኍል 29:16
7 Cross References  

የዮ​ሴ​ፍ​ንም ቀሚስ ወሰዱ፤ የፍ​የ​ልም ጠቦት አር​ደው ቀሚ​ሱን በደም ነከ​ሩት።


እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ቀ​ር​ቡት ቍር​ባን ይህ ነው፤ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሁለት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ዕለት ዕለት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


ለዐ​ሥራ አራቱ ጠቦ​ቶች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ፥


ከአ​ንዱ ጠቦ​ትም ጋር የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ ተወ​ቅጦ በተ​ጠ​ለለ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ታቀ​ር​ባ​ለህ።


የሠ​ራው ኀጢ​አት ቢታ​ወ​ቀ​ውና ንስሓ ቢገባ፥ ከፍ​የ​ሎች ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባት ፍየል ለቍ​ር​ባኑ ያቀ​ር​ባል፤


በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ሌላ፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ፥ በየ​ሰ​ን​በቱ ሁሉ የም​ታ​ቀ​ር​ቡት የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ይህ ነው።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ​ኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከመ​ጠጡ ቍር​ባን ሌላ ይቀ​ር​ባል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements