Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 28:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ለእ​ህል ቍር​ባ​ና​ቸው በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት፥ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ወይ​ፈን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአ​ን​ዱም አውራ በግ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ከእያንዳንዱም ወይፈን ጋራ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፉ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከአውራው በግ ጋራ የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት ይቀርባል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ለእህል ቁርባናቸው በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለእያንዳንዱ ወይፈን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአንዱም አውራ በግ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ተገቢ የሆነውንም የእህል ቊርባን በወይራ ዘይት የተለወሰ ምርጥ ዱቄት ታቀርባላችሁ፤ ይኸውም ከእያንዳንዱ ኰርማ ጋር ሦስት ኪሎ ዱቄት፥ ከአውራው በግ ጋር ሁለት ኪሎ ዱቄት፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ለእህል ቍርባናቸው በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለእያንዳንዱ ወይፈን ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአንዱም አውራ በግ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ፥

See the chapter Copy




ዘኍል 28:28
8 Cross References  

“በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ዓመት የሞ​ላ​ቸ​ውን ሁለት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ት​ንም አን​ዲት የዓ​መት እን​ስት የበግ ጠቦት፥ ስለ እህ​ልም ቍር​ባን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ፥ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት፥ አንድ ማሰሮ ዘይ​ትም ይወ​ስ​ዳል።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከላ​ሞች ሁለት በሬ​ዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥


ለሰ​ባ​ቱም ጠቦ​ቶች ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጠቦት ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ዐሥ​ረኛ እጅ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም በሙሴ ሕግ እንደ ተጻ​ፈው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በደ​ስ​ታና በመ​ዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የከ​ፈ​ላ​ቸ​ውን ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ሾመ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ እንደ ተጻፈ በጥ​ዋ​ትና በማታ በሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በመ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በበ​ዓ​ላ​ትም ለሚ​ቀ​ር​በው ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ንጉሡ ከገ​ን​ዘቡ የሚ​ከ​ፍ​ለ​ውን ወሰነ።


የኢ​ዮ​ሴ​ዴ​ቅም ልጅ ኢያሱ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ካህ​ናቱ፥ የሰ​ላ​ት​ያ​ልም ልጅ ዘሩ​ባ​ቤል፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ተነ​ሥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ መሠ​ዊያ ሠሩ።


ሞአ​ብ​ንና በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ላይ የሚ​ሠ​ዋ​ውን፥ ለአ​ማ​ል​ክ​ቱም የሚ​ያ​ጥ​ነ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በየ​በ​ዓ​ላ​ቱም፥ በየ​መ​ባ​ቻ​ውም፥ በየ​ሰ​ን​በ​ታ​ቱም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን መስ​ጠት በአ​ለ​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ እርሱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements