Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 28:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ቍር​ባ​ንና መሥ​ዋ​ዕት ሰባት ቀን በየ​ዕ​ለቱ እን​ዲሁ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከመ​ጠጡ ቍር​ባን ሌላ ይቀ​ር​ባል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በዚህም ዐይነት ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሆኖ በየዕለቱ ለሰባት ቀን በእሳት ለሚቀርብ መሥዋዕት የምግብ ቍርባን አዘጋጁ፤ ይህም ከመጠጥ ቍርባኑ ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋራ ሆኖ በተጨማሪ ይቀርባል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን የቁርባኑን ማዕድ ሰባት ቀን በየዕለቱ እንዲሁ ታቀርባላችሁ፤ ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቁርባን ጎን ለጎን የሚቀርብ ይሆናል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም የምግብ ቊርባን በተመሳሳይ ሁኔታ በሰባቱም ቀኖች ውስጥ ታቀርባላችሁ፤ ይህንንም የምታቀርቡት በቀኑ ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የመጠጥ መባ ጋር ተጨማሪ በማድረግ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚደረገውን የቍርባኑን መብል ሰባት ቀን በየዕለቱ እንዲሁ ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቍርባን ሌላ ይቀርባል።

See the chapter Copy




ዘኍል 28:24
5 Cross References  

ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ በጎ መዓዛ ያለው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።


እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ በእ​ሳት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ቀ​ር​ቡት ቍር​ባን ይህ ነው፤ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሁለት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ዕለት ዕለት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።


ከአ​ንዱ ጠቦ​ትም ጋር የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ ተወ​ቅጦ በተ​ጠ​ለለ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ታቀ​ር​ባ​ለህ።


በበ​ዓ​ሉም በሰ​ባቱ ቀኖች የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቅ​ርብ፤ ሰባ​ቱን ቀኖች በየ​ዕ​ለቱ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት ወይ​ፈ​ንና ሰባት አውራ በጎች ያቅ​ርብ፤ ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት በየ​ዕ​ለቱ ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ያቅ​ርብ።


ሊቀ ካህ​ና​ትም ሁሉ ዘወ​ትር እያ​ገ​ለ​ገለ ይቆም ነበር፤ ፈጽሞ ኀጢ​አት ማስ​ተ​ስ​ረይ የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ብቻም ይሠዋ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements