Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 27:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ​ዚህ በና​ባው አሻ​ገር ወዳ​ለው ተራራ ውጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ይገ​ዙ​አት ዘንድ እኔ የም​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እያት፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በዓባሪም ሸንተረር ላይ ወዳለው ወደዚህ ተራራ ውጣና ለእስራኤላውያን የሰጠኋቸውን ምድር እይ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደዚህ ወደ ዓባሪም ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች የሰጠኋትን ምድር እይ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ዐባሪም ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ልሰጣቸው ያቀድኩትን ምድር ሁሉ እይ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ወደዚህ ወደ ዓባሪም ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች የሰጠኋትን ምድር እይ፤

See the chapter Copy




ዘኍል 27:12
7 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የም​ት​ሞ​ት​በት ቀን እነሆ ቀረበ፤ ኢያ​ሱን ጠር​ተህ እር​ሱን አዝ​ዘው ዘንድ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር ቁም” አለው። ሙሴና ኢያ​ሱም ሄደው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ቆሙ።


ወዳ​ጆ​ችሽ ሁሉ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና ወደ ሊባ​ኖስ ወጥ​ተሽ ጩኺ፤ በባ​ሳ​ንም ላይ ድም​ፅ​ሽን አንሺ፤ በባ​ሕ​ሩም ማዶ ጩኺ።


በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ር​ባ​ትን ይህ​ችን ምድር፥ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ሁሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​አት ዘንድ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements