Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 27:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የአ​ባ​ቱም ወን​ድ​ሞች ባይ​ኖ​ሩት ከወ​ገኑ ለቀ​ረበ ዘመድ ርስ​ቱን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ እር​ሱም ይው​ረ​ሰው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ይሁን።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 አባቱ፣ ወንድሞች ከሌሉት ውርሱን ከጐሣው መካከል ቅርብ ለሆነ ዘመዱ ይስጥ፤ እርሱም ይውረሰው። ይህም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤላውያን ሕጋዊ መመሪያ ይሆናቸዋል።’ ”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አባቱም ወንድሞች ባይኖሩት ከወገኑ ለቀረበ ዘመድ ርስቱን ትሰጣላችሁ እርሱም ይውረሰው፤ ጌታም ሙሴን እንዳዘዘ ለእስራኤል ልጆች ሥርዓትና ፍርድ ይሁን።’ ”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ወንድሞችም ሆኑ አጐቶች ከሌሉት የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሰው ንብረቱን ወርሶ ሊጠቀምበት ይችላል፤ እኔ እግዚአብሔር ባዘዝኩህ መሠረት የእስራኤል ሕዝብ ይህን ሕግና ሥርዓት ቋሚ መመሪያ አድርገው ይጠብቁት።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የአባቱም ወንድሞች ባይኖሩት ከወገኑ ለቀረበ ዘመድ ርስቱን ስጡ እርሱም ይውረሰው፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘ ለእስራኤል ልጆች ሥርዓትና ፍርድ ይሁን።

See the chapter Copy




ዘኍል 27:11
7 Cross References  

“እነ​ዚ​ህም ነገ​ሮች ለልጅ ልጃ​ችሁ በማ​ደ​ሪ​ያ​ችሁ ሁሉ ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የአ​ጎቴ ልጅ አና​ም​ኤል እኔ ወደ አለ​ሁ​በት ወደ ግዞቱ ቤት አደ​ባ​ባይ መጥቶ፥ “በብ​ን​ያም ሀገር በዓ​ና​ቶት ያለ​ውን እር​ሻ​ዬን ግዛ፤ የመ​ግ​ዛ​ትና የመ​ው​ረስ መብቱ የአ​ንተ ነውና፥ አንተ ታላ​ቃ​ችን ነህና፤ ለአ​ንተ ግዛው” አለኝ። ይህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ።


ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ትና ሕግ ሆነ።


ወይም አጎቱ ወይም የአ​ጎቱ ልጅ ይቤ​ዠው፤ ወይም ከወ​ገኑ ለእ​ርሱ የቀ​ረበ ዘመድ ይቤ​ዠው፤ ወይም እርሱ እጁ ቢረ​ጥብ ራሱን ይቤ​ዠው።


ወን​ድ​ም​ህም ቢደ​ኸይ፥ ከር​ስ​ቱም ቢሸጥ፥ ለእ​ርሱ የቀ​ረበ ዘመዱ መጥቶ ወን​ድሙ የሸ​ጠ​ውን ይቤ​ዠ​ዋል።


ወን​ድ​ሞ​ችም ባይ​ኖ​ሩት፥ ርስ​ቱን ለአ​ባቱ ወን​ድ​ሞች ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements