Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 26:55 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

55 ነገር ግን ምድ​ሪቱ በየ​ስ​ማ​ቸው በዕጣ ትከ​ፋ​ፈ​ላ​ለች፤ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ነገድ ይወ​ር​ሳሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

55 የመሬት ድልድሉም በዕጣ ይሁን፤ እያንዳንዱ የሚወርሰውም በየነገድ አባቶቹ ስም ይሆናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

55 ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፋፈላለች፤ እንደ አባቶቻቸው ነገድ ስም ይወርሳሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

55 ሆኖም ክፍፍሉ የሚደረገው በዕጣ ነው፤ ዕጣውም የሚጣለው በየነገዱ መሠረት ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

55 ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፈላለች፤ እንደ አባቶቻቸው ነገድ ስም ይወርሳሉ።

See the chapter Copy




ዘኍል 26:55
21 Cross References  

ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ጠኙ ነገ​ድና ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ይሰ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ እንደ አዘዘ በዕጣ የም​ት​ወ​ር​ሱ​አት ምድር ይህች ናት፤


ምድ​ሪ​ቱ​ንም ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ትከ​ፋ​ፈ​ሏ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለብ​ዙ​ዎች ድር​ሻ​ቸ​ውን አብ​ዙ​ላ​ቸው፤ ለጥ​ቂ​ቶ​ችም ድር​ሻ​ቸ​ውን ጥቂት አድ​ርጉ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደ​ቀ​ለት በዚያ ርስቱ ይሆ​ናል፤ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ነገ​ዶች ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ ለዘ​ጠኙ ነገ​ድና ለእ​ኩ​ሌ​ታው በየ​ር​ስ​ታ​ቸው በዕጣ አከ​ፋ​ፈ​ሉ​አ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ክፍ​ላ​ቸው በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው፤ ምድ​ሪ​ቱም ከጦ​ር​ነት ዐረ​ፈች።


በብ​ር​ሃን ቅዱ​ሳን ለሚ​ታ​ደ​ሉት ርስት የበ​ቃን ያደ​ረ​ገ​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብን አመ​ስ​ግ​ኑት።


ዕጣም አጣ​ጣ​ሏ​ቸው፤ ዕጣ​ዉም በማ​ት​ያስ ላይ ወጣ፤ ከዐ​ሥራ አንዱ ሐዋ​ር​ያት ጋራም ተቈ​ጠረ።


ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥ በኀያላንም መካከል ይለያል።


የበደለኛ ሰው በደሉ ሁሉ ወደ ጕያው ይመለሳል። ጽድቅ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።


ሰባ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለዳን ልጆች ወጣ።


ስድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለን​ፍ​ታ​ሌም ልጆች ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ።


አም​ስ​ተ​ኛው ዕጣ ለአ​ሴር ልጆች ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ።


አራ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለይ​ሳ​ኮር ልጆች ወጣ።


ሦስ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለዛ​ብ​ሎን ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ፤ የር​ስ​ታ​ቸ​ውም ድን​በር እስከ ኤሴ​ዴቅ ጎላ ነበረ፤


ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዕጣ ለስ​ም​ዖን ልጆች ነገድ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ወጣ፤ ርስ​ታ​ቸ​ውም በይ​ሁዳ ልጆች ርስት መካ​ከል ነበረ።


እና​ን​ተም ምድ​ሪ​ቱን በሰ​ባት ክፍል ክፈ​ሏት፤ ወደ እኔም ወዲህ አም​ጡ​ልኝ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚህ ዕጣ አጣ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ኢያ​ሱን፥ “እኛ ብዙ ሕዝብ ስን​ሆን እስከ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ባረ​ከን ለምን አንድ ክፍል፥ አን​ድም ዕጣ ብቻ ርስት አድ​ር​ገህ ሰጠ​ኸን?” ብለው ወቀ​ሱት።


በብ​ዙ​ዎ​ችና በጥ​ቂ​ቶች መካ​ከል ርስ​ታ​ቸ​ውን በዕጣ ትከ​ፍ​ላ​ለህ።


ለእ​ና​ን​ተና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ለሚ​ቀ​መጡ፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ልጆ​ችን ለሚ​ወ​ልዱ መጻ​ተ​ኞች ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ በዕጣ ትካ​ፈ​ሉ​አ​ታ​ላ​ችሁ፤ እነ​ር​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል እንደ አሉ የሀ​ገር ልጆች ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች መካ​ከል ከእ​ና​ንተ ጋር ርስ​ትን ይወ​ር​ሳሉ።


“ምድ​ሪ​ቱን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት አድ​ርጎ በዕጣ ከፍሎ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጌታ​ች​ንን አዘ​ዘው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ን​ድ​ማ​ች​ንን የሰ​ለ​ጰ​ዓ​ድን ርስት ለሴ​ቶች ልጆቹ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ጌታ​ች​ንን አዘ​ዘው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements