ዘኍል 24:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 “የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ ተኝቶ ዐይኖቹ የተከፈቱለት እንዲህ ይላል፦ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 የዚያ የአምላክን ቃል የሚሰማ፣ ሁሉን ቻይ የአምላክን ራእይ የሚያይ፣ ከመሬት የተደፋው ዐይኖቹም የተከፈቱለት ሰው ንግር፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 የእግዚአብሔርን ቃላት የሚሰማ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ ወድቆም ሳለ ዐይኖቹ ግን የተከፈቱለት እንዲህ ይላል፦ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 የእግዚአብሔርን ቃላት የሚሰማ፥ ወድቆ ሳለ ዐይኖቹ ተከፍተው፥ ሁሉን የሚችል አምላክን ራእይ የሚያይ ሰው መልእክት ይህ ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ የወደቀው፥ ዓይኖቹም የተከፈቱለት እንዲህ ይላል፦ See the chapter |