ዘኍል 23:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ አንበሳ ደቦል ያገሣል፤ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አይተኛም።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይነሣል፤ ያደነውን እስኪያነክት፣ የገደለውንም ደም እስኪጠጣ፣ እንደማያርፍ አንበሳ ሆኖ ይነሣል።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ብድግ ይላል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አያርፍም።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 የእስራኤል ሕዝብ እንደ እንስት አንበሳ ይቆማል፤ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን ሳይበላና ደሙን ሳይጠጣ አያርፍም።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይቆማል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አይተኛም። See the chapter |
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛልና፥ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ እንደሚያገሣ፥ ድምፁም ተራሮችን እስኪሞላ በእርሱ ላይ እንደሚጮህ፥ እረኞችም ሁሉ ሲጮሁበት ከብዛታቸው የተነሣ እንደማይፈራ፥ ከድምፃቸውም የተነሣ እንደማይደነግጥ፥ እነርሱም ከቍጣው ብዛት የተነሣ ድል እንደሚሆኑና እንደሚደነግጡ፥ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።