Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 23:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ያወ​ጣው እርሱ ጕል​በቱ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ክብር ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እግዚአብሔር ከግብጽ አወጣቸው፤ ብርታታቸውም እንደ ጐሽ ብርታት ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከግብጽ ያወጣቸው እግዚአብሔር፥ ለእነርሱ እንደ ጎሽ ቀንድ ያለ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከግብጽ ምድር ያወጣቸው እግዚአብሔር እርሱ ለእነርሱ እንደ ጎሽ ቀንድ ይዋጋላቸዋል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶአቸዋል፤ ጕልበቱ አንድ ቀንድ እንዳለው ነው።

See the chapter Copy




ዘኍል 23:22
14 Cross References  

ውበቱ እንደ ላም በኵር ነው፤ ቀን​ዶቹ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ናቸው፤ በእ​ነ​ርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ሁሉ ይወ​ጋል፤ የኤ​ፍ​ሬም እልፍ አእ​ላ​ፋት፥ የም​ና​ሴም አእ​ላ​ፋት እነ​ርሱ ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ መርቶ አው​ጥ​ቶ​ታል፤ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ክብር አለው፤ ጠላ​ቶ​ቹን አሕ​ዛ​ብን ይበ​ላል፤ አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ባ​ብ​ራል፤ በፍ​ላ​ጾ​ቹም ጠላ​ቱን ይወ​ጋ​ዋል።


“ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ሁህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን አድ​ኗ​ታ​ልና፥ የይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ይሠ​ራ​ሉና፤ በዚ​ያም ይቀ​መ​ጣሉ ይወ​ር​ሷ​ታ​ልም።


በወ​ን​ዙም አጠ​ገብ ባለ​ችው በሕ​ዝቡ ልጆች ምድር በፋ​ቱራ ወደ ተቀ​መ​ጠው ወደ ቢዖር ልጅ ወደ በለ​ዓም፥ “እነሆ፥ ከግ​ብፅ የወጣ ሕዝብ አለ፤


ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም በፈ​ር​ዖ​ንና በሰ​ረ​ገ​ሎቹ፥ በፈ​ረ​ሰ​ኞ​ቹም ላይ ክብር በአ​ገ​ኘሁ ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


ነገር ግን ኀይ​ሌን እገ​ል​ጥ​ብህ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ላይ ይነ​ገር ዘንድ ስለ​ዚህ ጠበ​ቅ​ሁህ።


ከግ​ብፅ ምድር በወ​ጣ​ችሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በፊ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ደ​ረቀ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ በነ​በ​ሩት፥ እና​ን​ተም ፈጽ​ማ​ችሁ ባጠ​ፋ​ች​ኋ​ቸው በሁ​ለቱ በአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥ​ታት፥ በሴ​ዎ​ንና በዐግ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን ሰም​ተ​ናል።


ኀያ​ላን ከእ​ነ​ርሱ ጋር፥ ወይ​ፈ​ኖ​ችም ከኮ​ር​ማ​ዎች ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ ምድ​ራ​ቸ​ውም በደም ትሰ​ክ​ራ​ለች፤ በስ​ባ​ቸ​ውም ትወ​ፍ​ራ​ለች።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት ሁሉ በሌ​ሊት ከግ​ብፅ ምድር ወጣ።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements