Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 23:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በሜዳ ወደ ተገ​ነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰ​ደው፤ አዞ​ረ​ውም፤ ሰባ​ትም መሠ​ዊ​ያ​ዎች ሠራ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈን፥ አን​ድም አውራ በግ አሳ​ረገ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህም በፈስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወዳለው ወደ ጾፊም ሜዳ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያ ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ወደ ጾፊምም ሜዳ ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ ላይ ወሰደው፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን አንድም አውራ በግ አሳረገ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚያም በፒስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወደሚገኘው ወደ ጾፊም መስክ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያዎችን ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ወደ ጾፊምም ሜዳ ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ ላይ ወሰደው፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን አንድም አውራ በግ አሳረገ።

See the chapter Copy




ዘኍል 23:14
11 Cross References  

ለነ​ቢ​ያ​ትም ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ራእ​ይ​ንም አብ​ዝ​ቻ​ለሁ፤ በነ​ቢ​ያ​ትም እጅ ተመ​ስ​ያ​ለሁ።


ወር​ቁ​ንና ብሩን ከኮ​ሮጆ የሚ​ያ​ወ​ጡና በሚ​ዛን የሚ​መ​ዝኑ እነ​ርሱ አን​ጥ​ረ​ኛ​ውን ይቀ​ጥ​ራሉ፤ እር​ሱም ጣዖት አድ​ርጎ ይሠ​ራ​ዋል፤ ለዚ​ያም ይጐ​ነ​በ​ሱ​ለ​ታል፤ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ት​ማል።


ሙሴም ከሞ​ዓብ ሜዳ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ወዳ​ለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስከ ዳን ድረስ ያለ​ውን የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር አሳ​የው፤


በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ መሿ​ለ​ኪያ ካለው ከአ​ሴ​ዶን ተራራ በታች ያለ​ውን ዓረባ ሁሉ ወሰዱ።


ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን አት​ሻ​ገ​ር​ምና ወደ ተራ​ራው ራስ ውጣ፤ ዐይ​ን​ህ​ንም ወደ ባሕር ወደ መስ​ዕም፥ ወደ አዜ​ብም ወደ ምሥ​ራ​ቅም አን​ሥ​ተህ በዐ​ይ​ንህ ተመ​ል​ከት።


በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “በዚህ ሰባት መሠ​ዊ​ያ​ዎች ሥራ​ልኝ፤ በዚ​ህም ሰባት ወይ​ፈን፥ ሰባ​ትም አውራ በግ አዘ​ጋ​ጅ​ልኝ” አለው።


ከባ​ሞ​ትም ምድረ በዳ​ውን ከላይ ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ በሞ​ዓብ በረሃ ወዳ​ለው ወደ ያኒን ሸለቆ ተጓዙ።


ባላ​ቅም፥ “በዚያ እነ​ር​ሱን ወደ​ማ​ታ​ይ​በት ወደ ሌላ ቦታ እባ​ክህ፥ ከእኔ ጋር ና፤ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዱን ወገን ብቻ ታያ​ለህ፤ ሁሉን ግን አታ​ይም፤ በዚ​ያም እነ​ር​ሱን ርገ​ም​ልኝ” አለው።


በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን አለው፥ “በዚህ በመ​ሥ​ዋ​ዕ​ትህ ዘንድ ቈይ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጠ​ይቅ ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements