ዘኍል 22:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 እርሱም ስለ ሄደ እግዚአብሔር ተቈጣ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ሊያሰናክለው ተነሣ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ይሁን እንጂ በለዓም በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር በጣም ተቈጥቶ ስለ ነበር የእግዚአብሔር መልአክ ሊቃወመው በመንገዱ ላይ ቆመ። በለዓምም በአህያው ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ሁለት አሽከሮቹም ዐብረው ነበሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 እርሱም ስለ ሄደ እግዚአብሔር ተቈጣ፤ የጌታም መልአክ ሊቃወመው በመንገድ ላይ ቆመ። እርሱም በአህያይቱ ላይ ሆኖ ይጓዝ ነበር፥ ሁለቱም ሎሌዎቹ ከእርሱ ጋር ነበሩ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 በለዓም በመሄዱ እግዚአብሔር ተቈጣ፤ በለዓም ሁለቱን አሽከሮቹን በማስከተል በአህያው ላይ ተቀምጦ በሚጓዝበት ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በፊቱ ቆሞ መንገዱን ዘጋበት፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 እርሱም ስለ ሄደ እግዚአብሔር ተቈጣ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ሊቍቍመው በመንገድ ላይ ቆመ። እርሱም በአህያይቱ ላይ፥ ሁለቱም ሎሌዎቹ ከእርሱ ጋር ነበሩ። See the chapter |