Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 21:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 እር​ሱ​ንና ልጆ​ቹን፥ ሕዝ​ቡን ሁሉ አንድ ሰው ሳያ​መ​ልጥ መቱ፤ ምድ​ሩ​ንም ወረሱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ስለዚህም እስራኤላውያን ዐግን ከልጆቹና ከመላው ሰራዊቱ ጋራ አንድም ሳይቀሩ ሁሉንም አጠፏቸው፤ ምድሩንም ወረሱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ለእርሱም አንድ ሰው በሕይወት እንዳይተርፍ አድርገው እርሱንና ልጆቹን ሕዝቡንም ሁሉ ገደሉ፤ ምድሩንም ወረሱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ስለዚህ እስራኤላውያን ዖግን፥ ልጆቹን፥ ሕዝቡን ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ ፈጅተው ምድሩን ወረሱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 እርሱንና ልጆቹን ሕዝቡንም ሁሉ መቱ ሰውም አልቀረለትም፤ ምድሩንም ወረሱ።

See the chapter Copy




ዘኍል 21:35
13 Cross References  

በባ​ሳን የነ​በ​ረ​ውን፥ በአ​ስ​ታ​ሮ​ትና በኤ​ን​ድ​ራ​ይን የነ​ገ​ሠ​ውን የዐ​ግን መን​ግ​ሥት ሁሉ፤ እር​ሱም ከረ​ዓ​ይት የቀረ ነበረ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ሙሴ አወ​ጣ​ቸው፤ ገደ​ላ​ቸ​ውም።


ነገር ግን በወ​ደ​ደን በእ​ርሱ ሁሉን ድል እን​ነ​ሣ​ለን።


ሖራ​ው​ያ​ንም ደግሞ አስ​ቀ​ድሞ በሴ​ይር ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ የዔ​ሳው ልጆች ግን መቱ​አ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ጠው በር​ስቱ ምድር እስ​ራ​ኤል እን​ዳ​ደ​ረገ፥ በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የሰ​ጣት ምድር የከ​ብት መሰ​ማ​ሪያ ሀገር ናት፤ ለእ​ኛም ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ብዙ እን​ስ​ሳት አሉን።


ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ቱት፥ በሐ​ሴ​ቦን ተቀ​ምጦ በነ​በ​ረው በአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ በሴ​ዎን ምድር፥ በቤተ ፌጎር አቅ​ራ​ቢያ ባለው ሸለቆ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ፤


የእ​ር​ሱ​ንና የባ​ሳ​ንን ንጉሥ፥ የዐ​ግን ምድር፥ በም​ሥ​ራቅ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ የነ​በ​ሩ​ትን የሁ​ለ​ቱን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ንን ነገ​ሥ​ታት ምድር ወሰዱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ባጠ​ፋ​ቸው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሚ​ኖሩ በሁ​ለቱ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ነገ​ሥ​ታት በሴ​ዎ​ንና በዐግ፥ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም እን​ዳ​ደ​ረገ እን​ዲሁ ያደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አላ​ቸው፥ “ግብ​ፃ​ው​ያን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ የአ​ሞ​ንና የሞ​አ​ብም ልጆች፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements