Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 21:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን፥ “ሕዝ​ቡን ሰብ​ስብ፤ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ” ብሎ ወደ ተና​ገ​ረ​ላት ጕድ​ጓድ ሄዱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያም እግዚአብሔር ለሙሴ፣ “ሰዎቹን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” ወዳለበት ብኤር ወደተባለው የውሃ ጕድጓድ ጕዟቸውን ቀጠሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ፤ ይኸውም ጌታ ሙሴን፦ “ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ” ብሎ የተናገረለት ጉድጓድ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚያም ተነሥተው “የውሃ ጒድጓዶች” ወደ ተባለው ስፍራ ሄዱ፤ በእዚያም እግዚአብሔር ሙሴን “ሕዝቡን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከዚያም ወደ ብኤር ተጓዙ፤ ይኸውም እግዚአብሔር ሙሴን፦ ሕዝቡን ሰብስብ ውኃንም እሰጣቸዋለሁ ብሎ የተናገረለት ጕድጓድ ነው።

See the chapter Copy




ዘኍል 21:16
16 Cross References  

“ይህ​ችን በት​ር​ህን ውሰድ፤ አን​ተና ወን​ድ​ምህ አሮ​ንም ማኅ​በ​ሩን ሰብ​ስቡ፤ ዐለ​ቷ​ንም በፊ​ታ​ቸው እዘ​ዟት፤ ውኃ ትሰ​ጣ​ለች፤ ከድ​ን​ጋ​ይ​ዋም ውኃ ታወ​ጡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ እን​ዲ​ሁም ማኅ​በ​ሩን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታጠ​ጡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።”


ውኃ​ው​ንም ከሕ​ይ​ወት ምን​ጮች በደ​ስታ ትቀ​ዳ​ላ​ችሁ።


መንፈሱና ሙሽራይቱም “ና!” ይላሉ። የሚሰማም “ና!” ይበል። የተጠማም ይምጣ፤ የወደደም የሕይወትን ውሃ እንዲያው ይውሰድ።


በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውሃ ወንዝ አሳየኝ።


አለኝም “ተፈጽሞአል፤ አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውሃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።


የም​ድረ በዳ አራ​ዊት፥ ቀበ​ሮ​ችና ሰጎ​ኖች፥ ያከ​ብ​ሩ​ኛል። የመ​ረ​ጥ​ሁ​ትን ሕዝ​ቤን አጠጣ ዘንድ በም​ድረ በዳ ውኃን፥ በበ​ረ​ሃም ወን​ዞ​ችን ሰጥ​ቻ​ለ​ሁና፤


ኢዮ​አ​ታ​ምም ሸሽቶ አመ​ለጠ፤ ወን​ድ​ሙን አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ፈርቶ ወደ ብኤር ሄደ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጠ።


እነሆ፥ እኔ በዚያ በኮ​ሬብ በዓ​ለት ላይ በፊ​ትህ እቆ​ማ​ለሁ፤ ዓለ​ቱ​ንም ትመ​ታ​ለህ፤ ሕዝ​ቡም ይጠጣ ዘንድ ከእ​ርሱ ውኃ ይወ​ጣል” አለው። ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዲሁ አደ​ረገ።


እኔ ከም​ሰ​ጠው ውኃ የሚ​ጠጣ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም፤ እኔ የም​ሰ​ጠው ውኃ በው​ስጡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የሚ​ፈ​ልቅ የውኃ ምንጭ ይሆ​ን​ለ​ታል እንጂ።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦ​ታና ውኃ አጠ​ጪኝ ብሎ የሚ​ለ​ም​ንሽ ማን እንደ ሆነ ብታ​ው​ቂስ አንቺ ደግሞ በለ​መ​ን​ሺው ነበር፤ እር​ሱም የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ በሰ​ጠሽ ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላት።


የሚ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም ያጽ​ና​ና​ቸ​ዋ​ልና፥ በውኃ ምን​ጮ​ችም በኩል ይመ​ራ​ቸ​ዋ​ልና አይ​ራ​ቡም፤ አይ​ጠ​ሙም፤ የፀ​ሐይ ትኩ​ሳ​ትም አይ​ጐ​ዳ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ጋር ዐይ​ን​ዋን ከፈ​ተ​ላት፤ የውኃ ጕድ​ጓ​ድ​ንም አየች፤ ሄዳም አቍ​ማ​ዳ​ውን በውኃ ሞላች፤ ልጅ​ዋ​ንም አጠ​ጣ​ችው።


ከዲ​ቦ​ን​ጋ​ድም ተጕ​ዘው በጌ​ል​ሞ​ን​ዲ​ብ​ላ​ታ​ይም ሰፈሩ።


ጩኸት የሞ​ዓ​ብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፤ ልቅ​ሶ​ዋም ወደ ኤግ​ላ​ይ​ምና ወደ ኢሊም ጕድ​ጓድ ደረሰ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements