Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 20:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዘር ወደ​ማ​ይ​ዘ​ራ​በት፥ በለ​ስና ወይ​ንም፥ ሮማ​ንም፥ የሚ​ጠ​ጣም ውኃ ወደ​ሌ​ለ​በት ወደ​ዚህ ክፉ ስፍራ ታመ​ጡን ዘንድ ከግ​ብፅ ለምን አወ​ጣ​ች​ሁን?”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከግብጽ አውጥታችሁ እህል ወይም በለስ፣ ወይን ወይም ሮማን ወደሌለበት ወደዚህ ክፉ ቦታ ያመጣችሁንስ ለምንድን ነው? የሚጠጣ ውሃ እንኳ ይታጣ!”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ወደዚህ ክፉ ስፍራ ልታመጡን ከግብጽ ለምን አወጣችሁን? ለዘርና ለበለስ ለወይንም ለሮማንም የማይሆን ስፍራ ነው፤ የሚጠጣም ውኃ የለበትም።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከግብጽ አውጥታችሁ ምንም ነገር ወደማይበቅልበት ወደዚህ አስከፊ ምድር ለምን አመጣችሁን? በዚህ ስፍራ እህል፥ በለስ፥ ወይንና ሮማን አይገኝም፤ ሌላው ቀርቶ የሚጠጣ ውሃ እንኳ የለም!”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ወደዚህ ክፉ ስፍራ ታመጡን ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን? ዘርና በለስ ወይንም ሮማንም የሌለበት ስፍራ ነው፤ የሚጠጣም ውኃ የለበትም።

See the chapter Copy




ዘኍል 20:5
8 Cross References  

አንተ አለቃ ነህን? ደግ​ሞስ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ምድር አገ​ባ​ኸ​ንን? እር​ሻ​ንና የወ​ይን ቦታ​ንስ አወ​ረ​ስ​ኸ​ንን? የእ​ነ​ዚ​ህ​ንስ ሰዎች ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ታወ​ጣ​ለ​ህን? አን​መ​ጣም” አሉ።


በግ​ብፅ ምድረ በዳ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ጋር እንደ ተፋ​ረ​ድሁ እን​ዲሁ ከእ​ና​ንተ ጋር እፋ​ረ​ዳ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እነ​ር​ሱም፥ “ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን፥ በም​ድረ በዳና በባ​ድማ፥ ዕን​ጨ​ትና ውኃ፥ የእ​ን​ጨት ፍሬም በሌ​ለ​በት ምድር፥ ሰው በማ​ያ​ል​ፍ​በ​ትና የሰው ልጅም በማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​በት ምድር የመ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት አለ? አላ​ሉም።


“ሂድ፤ እን​ዲህ ብለህ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጆሮ ተና​ገር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ት​ሽን ምሕ​ረት፥ የታ​ጨ​ሽ​በ​ት​ንም ፍቅር፥ በም​ድረ በዳ ዘር ባል​ተ​ዘ​ራ​በት ምድር እንደ ተከ​ተ​ል​ሽኝ አስ​ቤ​አ​ለሁ።


አርባ ዓመ​ትም በም​ድረ በዳ መገ​ብ​ሃ​ቸው፤ ምንም አላ​ሳ​ጣ​ሃ​ቸ​ውም፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም አላ​ረ​ጀም፤ እግ​ራ​ቸ​ውም አላ​በ​ጠም።


የሚ​ና​ደፍ እባ​ብና ጊንጥ፥ ጥማ​ትም ባለ​ባት፥ ውኃም በሌ​ለ​ባት፥ በታ​ላ​ቂ​ቱና በም​ታ​ስ​ፈ​ራው ምድረ በዳ የመ​ራ​ህን፥ ከጭ​ንጫ ድን​ጋ​ይም ጣፋጭ ውኃን ያወ​ጣ​ል​ህን፥


“አሮን ወደ ወገኑ ይጨ​መር፤ በክ​ር​ክር ውኃ ዘንድ ስለ አሳ​ዘ​ና​ች​ሁኝ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ሰጠ​ኋት ምድር አት​ገ​ቡም።


እና​ንተ በጺን ምድረ በዳ በማ​ኅ​በሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐም​ፃ​ች​ኋ​ልና፥ በእ​ነ​ር​ሱም ፊት በው​ኃው ዘንድ አላ​ከ​በ​ራ​ች​ሁ​ኝ​ምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃ​ዴስ ያለው የክ​ር​ክር ውኃ ነው።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements