Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 20:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ እስ​ራ​ኤል በዳ​ር​ቻው እን​ዲ​ያ​ልፍ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤል ከእ​ርሱ ተመ​ለሰ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ስለዚህ ኤዶም በግዛቱ ዐልፈው እንዳይሄዱ ስለ ከለከላቸው እስራኤላውያን ተመለሱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ኤዶምያስም እስራኤል በግዛቱ ውስጥ እንዳያልፍ ከለከለ፤ ስለዚህ እስራኤል ከእርሱ ተመለሰ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ኤዶማውያን እስራኤላውያን በግዛታቸው አልፈው እንዳይሄዱ በመከልከላቸው ምክንያት እስራኤላውያን መንገድ ለውጠው በሌላ በኩል ሄዱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ኤዶምያስም በብዙ ሕዝብና በጽኑ እጅ ሊገጥመው ወጣ። ኤዶምያስም እስራኤል በዳርቻው እንዳያልፍ ከለከለ፤ ስለዚህ እስራኤል ከእርሱ ተመለሰ።

See the chapter Copy




ዘኍል 20:21
10 Cross References  

እስ​ራ​ኤ​ልም በቃ​ዴስ ተቀ​መጠ። በም​ድረ በዳም በኩል አለፈ፤ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንና የሞ​ዓ​ብ​ንም ምድር ዞሩ፤ ከሞ​ዓብ ምድ​ርም በም​ሥ​ራቅ በኩል መጡ፤ በአ​ር​ኖ​ንም ማዶ ሰፈሩ፤ አር​ኖ​ንም የሞ​ዓብ ድን​በር ነበ​ረና ወደ ሞዓብ ድን​በር አል​ገ​ቡም።


በሴ​ይር የተ​ቀ​መጡ የዔ​ሳው ልጆች፥ በአ​ሮ​ዔ​ርም የተ​ቀ​መጡ ሞዓ​ባ​ው​ያን እን​ዳ​ደ​ረ​ጉ​ልኝ፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጠን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን እስ​ክ​ሻ​ገር ድረስ በእ​ግሬ ልለፍ።


አም​ላ​ክህ ኮሞስ የሚ​ሰ​ጥ​ህን የም​ት​ወ​ርስ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? እኛም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ታ​ችን ያስ​ወ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ነ​ር​ሱን ምድር የም​ን​ወ​ርስ አይ​ደ​ለ​ን​ምን?


“ኤዶ​ማ​ዊዉ ወን​ድ​ምህ ነውና አት​ጸ​የ​ፈው፤ ግብ​ፃ​ዊ​ዉ​ንም በሀ​ገሩ ስደ​ተኛ ነበ​ር​ህና አት​ጸ​የ​ፈው።


‘በሀ​ገ​ርህ ላይ ልለፍ፤ በአ​ውራ ጎዳና እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አል​ተ​ላ​ለ​ፍም።


ሴዎ​ንም እስ​ራ​ኤል በወ​ሰኑ ላይ ያልፉ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ሴዎ​ንም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ለመ​ው​ጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፤ ወደ ኢያ​ሶ​ንም መጣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ተዋ​ጋ​ቸው።


እስ​ራ​ኤል ወደ ኤዶ​ም​ያስ ንጉሥ፦ ‘በም​ድ​ርህ እን​ዳ​ልፍ፥ እባ​ክህ፥ ፍቀ​ድ​ልኝ’ ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ እንቢ አለ። እን​ዲ​ሁም ወደ ሞዓብ ንጉሥ ላከ፤ እር​ሱም እንቢ አለ።


ከሖ​ርም ተራራ በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ተጓዙ፤ የኤ​ዶ​ም​ንም ምድር ዞሩ​አት፤ ሕዝ​ቡም በመ​ን​ገድ ተበ​ሳጩ።


አሁ​ንም እነሆ፥ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብዕ ምድር በወጡ ጊዜ ያል​ፉ​ባ​ቸው ዘንድ ያል​ፈ​ቀ​ድ​ህ​ላ​ቸው የአ​ሞ​ንና የሞ​ዓብ ልጆች፥ የሴ​ይ​ርም ተራራ ሰዎች እን​ዳ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ፈቀቅ ብለው ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements