Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 20:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተከ​ራ​ክ​ረ​ው​በ​ታ​ልና ይህ ውኃ የክ​ር​ክር ውኃ ተባለ። እር​ሱም ቅዱስ መሆኑ የተ​ገ​ለ​ጠ​በት ይህ የክ​ር​ክር ውኃ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ጋራ የተጣሉበት፣ እርሱም ቅዱስ መሆኑን በመካከላቸው የገለጠበት ይህ የመሪባ ውሃ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የእስራኤል ልጆች ከጌታ ጋር የተጣሉበት፥ እርሱም በመካከላቸው ቅዱስ መሆኑን የገለጠበት ይህ የመሪባ ውኃ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የእስራኤል ሕዝብ ከእግዚአብሔር ጋር የተጣሉበትና እርሱም የቅድስናውን ክብር የገለጠበት ስፍራ መሪባ ስለ ተባለ ውሃውም የመሪባ ውሃ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ላይ ጠብ ያደረጉበት፥ እርሱም ቅዱስ መሆኑን የገለጠበት ይህ የመሪባ ውኃ ነው።

See the chapter Copy




ዘኍል 20:13
11 Cross References  

ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለስሙ ክብ​ርን አምጡ፤ መሥ​ዋ​ዕት ያዙ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ችም ግቡ።


ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ክር​ክር፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ነውን? ወይስ አይ​ደ​ለም?” ሲሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑት የዚ​ያን ስፍራ ስም “መን​ሱት” ደግ​ሞም “ጋእዝ” ብሎ ጠራው።


ስለ ሌዊም እን​ዲህ አለ፥ ለሌዊ ቃሉን፥ በመ​ከ​ራም ለፈ​ተ​ኑት፥ በክ​ር​ክር ውኃም ለሰ​ደ​ቡት፥ ለእ​ው​ነ​ተ​ኛው ሰው ጽድ​ቁን መልስ።


በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል በጺን ምድረ በዳ በቃ​ዴስ ባለው በክ​ር​ክር ውኃ ለቃሌ አል​ታ​ዘ​ዛ​ች​ሁ​ምና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል አል​ቀ​ደ​ሳ​ች​ሁ​ኝ​ምና፥


ምድ​ር​ንም ትሸ​ፍን ዘንድ እንደ ደመና በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትወ​ጣ​ለህ። በኋ​ለ​ኛው ዘመን ይሆ​ናል፤ ጎግ ሆይ! በፊ​ታ​ቸው በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ብህ ጊዜ፥ አሕ​ዛብ ያው​ቁኝ ዘንድ በም​ድሬ ላይ አወ​ጣ​ሃ​ለሁ።


በአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ የረ​ከ​ሰ​ውን፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያረ​ከ​ሳ​ች​ሁ​ትን ገናና ስሜን እቀ​ድ​ሰ​ዋ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ና​ቸ​ውም ዘንድ በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ባ​ችሁ ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ አሕ​ዛብ ያው​ቃሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ባወ​ጣ​ኋ​ችሁ ጊዜ፥ ከተ​በ​ተ​ና​ች​ሁ​ባ​ትም ሀገር ሁሉ በሰ​በ​ሰ​ብ​ኋ​ችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት እቀ​ደ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በፍ​ርድ ከፍ ከፍ ይላል፤ ቅዱ​ሱም አም​ላክ በጽ​ድቅ ይከ​ብ​ራል።


እና​ንተ ግን እንደ ሰው ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፥ ከአ​ለ​ቆ​ችም እንደ አንዱ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ።


አቤቱ፥ ተነሥ፥ በም​ድር ላይ ፍረድ፥ አንተ አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ትወ​ር​ሳ​ለ​ህና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements