Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 19:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ርኩ​ሱም የሚ​ነ​ካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆ​ናል፤ የሚ​ነ​ካ​ውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የረከሰ ሰው የሚነካው ማንኛውም ነገር ይረክሳል፤ ይህን የነካ ሰው ደግሞ እስከ ማምሻው ድረስ የረከሰ ይሆናል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የረከሰውም ሰው የሚነካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ የሚነካውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ያልነጻ ሰው የሚነካው ነገር ሁሉ የረከሰ ይሆናል፤ ያንንም ዕቃ የሚነካ ሌላ ሰው እስከ ማታ እንደ ረከሰ ይቈያል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ርኩሱም የሚነካው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ የሚነካውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

See the chapter Copy




ዘኍል 19:22
21 Cross References  

ሐጌም፦ በሬሳ የረከሰ ሰው ከእነዚህ አንዱን ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይረክሳልን? አለ። ካህናቱም፦ አዎን ይረክሳል ብለው መለሱ።


“ርኩስ ነገር የሚ​ነ​ካ​ውን ሥጋ አይ​ብ​ሉት፤ በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉት እንጂ። ንጹሕ የሆነ ሰው ሁሉ ግን ከሥ​ጋው ይብላ።


መኝ​ታ​ው​ንም የሚ​ነካ ሰው ሁሉ ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ሰው​ነ​ቱን ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።


ርኩስ ነገ​ርን፥ የሞ​ተ​ውን፥ አውሬ የነ​ከ​ሰ​ውን፥ ወይም የበ​ከተ፥ ወይም የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የእ​ን​ስ​ሳን በድን የነካ፥ ከእ​ር​ሱም ያነሣ ሰው ቢኖር፤


ወይም ርኩ​ስ​ነ​ቱን ሳያ​ውቅ ርኩ​ስን ሰው ቢነካ፥ በማ​ና​ቸ​ውም ርኵ​ሰት ቢረ​ክስ፥ ነገሩ በታ​ወቀ ጊዜ በደል ይሆ​ን​በ​ታል።


ከር​ኩስ ሁሉ፥ ወይም ከረ​ከ​ሰው ሰው፥ ወይም ንጹሕ ካል​ሆ​ነው እን​ስሳ የነ​ካች ሰው​ነት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ ብት​በላ፥ ያች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።”


ወይም የሚ​ያ​ረ​ክ​ሰ​ውን ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ፥ ወይም በሁሉ ዐይ​ነት የረ​ከ​ሰ​ውን ሰው የሚ​ነካ፥


እነ​ዚ​ህን ሁሉ የሚ​ነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል፤ ገላ​ውን በውኃ ካል​ታ​ጠበ ከተ​ቀ​ደ​ሰው አይ​ብላ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፥


ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው በተ​ቀ​መ​ጠ​በት ነገር ላይ የሚ​ቀ​መ​ጥ​በት ሰው ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።


ፈሳሽ ነገር ያለ​በ​ትን የሰ​ውን ሥጋ የሚ​ነካ ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።


ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው በን​ጹሕ ሰው ላይ ቢተፋ ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።


ከበ​ታ​ቹም ያለ​ውን ነገር የሚ​ነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ነገ​ሮች የሚ​ያ​ነሣ ሁሉ ልብ​ሱን ይጠብ፤ በው​ኃም ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።


ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው እጁን በውኃ ሳይ​ታ​ጠብ የሚ​ነ​ካው ሁሉ ልብ​ሶ​ቹን ይጠብ፤ በው​ኃም ይታ​ጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


መኝ​ታ​ዋ​ንም የሚ​ነካ ሁሉ ልብ​ሶ​ቹን ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ሰው​ነ​ቱን ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።


የም​ት​ቀ​መ​ጥ​በ​ት​ንም ነገር ሁሉ የሚ​ነካ ሁሉ ልብ​ሶ​ቹን ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ሰው​ነ​ቱን ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


በመ​ኝ​ታ​ዋም ላይ ወይም በም​ት​ቀ​መ​ጥ​በት ነገር ላይ ቢሆን ሲነ​ካው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።


እነ​ዚ​ህ​ንም ነገ​ሮች የሚ​ነካ ሁሉ ርኩስ ነው፤ ልብ​ሱ​ንም ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


ካህ​ኑም ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውሃ ይታ​ጠ​ባል፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገ​ባል፤ ካህ​ኑም እስከ ማታ ርኩስ ይሆ​ናል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements