ዘኍል 19:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 “ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለመናውንም ባያነጻ፥ ያ ሰው የእግዚአብሔርን መቅደስ አርክሶአልና ከማኅበሩ መካከል ተለይቶ ይጠፋል፤ በሚያነጻ ውኃ አልተረጨምና ርኩስ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ይሁን እንጂ አንድ የረከሰ ሰው ራሱን ሳያነጻ ከቀረ የእግዚአብሔርን መቅደስ አርክሷልና ከማኅበረ ሰቡ ተለይቶ ይጥፋ፤ የሚያነጻው ውሃ ያልተረጨበት ስለ ሆነ ርኩስ ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 “ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለመናውንም ባያነጻ፥ ያ ሰው የጌታን መቅደስ አርክሶአልና ከጉባኤው መካከል ተለይቶ ይጠፋል፤ ከርኩሰት የሚያነጻውን ውኃ አልተረጨም፤ ርኩስ ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 “ያልነጻና ራሱንም ያላነጻ ሰው ለማንጻት የተመደበው ውሃ በላዩ ስላልፈሰሰ የረከሰ ሆኖ ይቈያል፤ እንደዚህ ያለው ሰው የእግዚአብሔርን ድንኳን ስለሚያረክስ ከማኅበሩ ይለይ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለመናውንም ባይጠራ፥ ያ ሰው የእግዚአብሔርን መቅደስ አርክሶአልና ከጉባኤው መካከል ተለይቶ ይጠፋል፤ በሚያነጻ ውኃ አልተረጨም፤ ርኩስ ነው። See the chapter |