Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 19:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ንጹ​ሕም ሰው ሂሶ​ጱን ወስዶ በው​ኃው ውስጥ ያጠ​ል​ቀ​ዋል፤ በቤ​ቱም፥ በዕ​ቃ​ውም ሁሉ፥ በዚ​ያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ አጥ​ን​ቱ​ንም ወይም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን፥ ወይም የሞ​ተ​ውን፥ ወይም መቃ​ብ​ሩን በነ​ካው ላይ ይረ​ጨ​ዋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆነ ሰው ሂሶጵ ወስዶ በውሃው ውስጥ ከነከረው በኋላ ድንኳኑን፣ በውስጡ ያሉትን ዕቃዎች ሁሉ፣ እዚያ የነበሩትንም ሰዎች ሁሉ ይርጫቸው። እንዲሁም የሰው ዐፅም ወይም መቃብር ወይም ደግሞ የተገደለውን ወይም እንዲሁ የሞተውን ሰው የነካው ማንኛውንም ሰው ይርጭ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ንጹሕም ሰው ሂሶጱን ወስዶ በውኃው ውስጥ ይነክረዋል፤ በድንኳኑም፥ በዕቃውም ሁሉ፥ በዚያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ ዐፅሙንም ወይም የተገደለውን ወይም የሞተውን ወይም መቃብሩን በነካው ሰው ላይ ይረጨዋል፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ቀጥሎም ንጹሕ የሆነ ሰው የሂሶጵ ቅርንጫፍ ወስዶ በውሃው ውስጥ እየነከረ በድንኳኑና በውስጡ በሚገኙት ዕቃዎች ሁሉ ላይ እንዲሁም በድንኳኑ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ላይ ይርጨው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ የሆነ ሰው ዐፅም ወይም ሬሳ ወይም መቃብር በነካው ሰው ላይ ውሃ ይርጭበት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ንጹሕም ሰው ሂሶጱን ወስዶ በውኃው ውስጥ ያጠልቀዋል፤ በድንኳኑም፥ በዕቃውም ሁሉ፥ በዚያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ አጥንቱንም ወይም የተገደለውን ወይም የሞተውን ወይም መቃብሩን በነካው ላይ ይረጨዋል፤

See the chapter Copy




ዘኍል 19:18
13 Cross References  

ነውር የሌ​ለው ሆኖ፥ በዘ​ለ​ዓ​ለም መን​ፈስ ራሱን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረበ የክ​ር​ስ​ቶስ ደም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ከው ዘንድ ሕሊ​ና​ች​ንን ከሞት ሥራ እን​ዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?


ንጹ​ሕም ሰው የጊ​ደ​ሪ​ቱን አመድ ያከ​ማ​ቻል፤ ከሰ​ፈ​ሩም ውጭ በን​ጹሕ ስፍራ ያኖ​ረ​ዋል፤ ርኵ​ሰት ለሚ​ያ​ነጻ ውኃ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ይጠ​በ​ቃል፤ ይነ​ጹ​በ​ታ​ልና።


እና​ን​ተም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ርሱ ናችሁ፤ በእ​ር​ሱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ጽድ​ቅን፥ ቅድ​ስ​ና​ንና ቤዛ​ነ​ትን አገ​ኘን።


እነ​ር​ሱም በእ​ው​ነት ቅዱ​ሳን ይሆኑ ዘንድ ስለ እነ​ርሱ እኔ ራሴን እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።


በእ​ው​ነ​ትህ ቀድ​ሳ​ቸው፤ ቃልህ እው​ነት ነውና።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረዳቱ ያላ​ደ​ረገ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ቱም ብዛት የታ​መነ፥ በከ​ንቱ ነገ​ርም የበ​ረታ ያ ሰው እነሆ።”


ሙሴ የኦ​ሪ​ትን ትእ​ዛዝ ሁሉ ለመ​ላው ሕዝብ ከነ​ገረ በኋላ፥ የላ​ምና የፍ​የል ደም ከውኃ ጋር ቀላ​ቅሎ፥ ቀይ የበግ ጠጕ​ርና የስ​ሚዛ ቅጠል ነክሮ መጽ​ሐፈ ኦሪ​ቱ​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ ይረጭ ነበር።


ለአ​ን​ጽሖ እን​ድ​ት​ሆን ከተ​ቃ​ጠ​ለ​ችው ጊደር አመድ ለር​ኩሱ ይወ​ስ​ዱ​ለ​ታል፤ በዕ​ቃ​ውም ውስጥ የም​ንጭ ውኃ ይቀ​ላ​ቅ​ሉ​በ​ታል።


ንጹ​ሑም በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀንና በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን በር​ኩሱ ላይ ይረ​ጨ​ዋል፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ይነ​ጻል፤ እር​ሱም ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በውኃ ይታ​ጠ​ባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።


ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ እር​ሱን ያደ​ን​ቃሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትም አፋ​ቸ​ውን ይዘ​ጋሉ፤ ስለ እርሱ ያል​ተ​ወ​ራ​ላ​ቸው ያው​ቁ​ታ​ልና፥ ያል​ሰ​ሙ​ትም ያስ​ተ​ው​ሉ​ታ​ልና።


አድ​ር​ገ​ህ​ል​ኛ​ልና ለዘ​ለ​ዓ​ለም አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ በጻ​ድ​ቃ​ን​ህም ዘንድ መል​ካም ነውና ምሕ​ረ​ት​ህን ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements