Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ለአ​ን​ጽሖ እን​ድ​ት​ሆን ከተ​ቃ​ጠ​ለ​ችው ጊደር አመድ ለር​ኩሱ ይወ​ስ​ዱ​ለ​ታል፤ በዕ​ቃ​ውም ውስጥ የም​ንጭ ውኃ ይቀ​ላ​ቅ​ሉ​በ​ታል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ለረከሰውም ሰው፣ ለማንጻት ከተቃጠለው የጊደር ዐመድ ላይ ማሰሮ ውስጥ በማድረግ በላዩ የምንጭ ውሃ ይጨምሩበት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከኃጢአት ለማንጻት እንድትሆን ከተቃጠለችው ጊደር አመድ ለረከሰው ሰው ይወስዱለታል፥ በዕቃውም ውስጥ የምንጭ ውኃ ይጨመርበታል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “ርኲሰቱንም ለማስወገድ፥ ለኃጢአት ማስተስረያ ከተቃጠለችው ጊደር ዐመድ ጥቂት ተወስዶ በማሰሮ ውስጥ ይከተት፤ ንጹሕ የምንጭ ውሃም ይጨመርበት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከኃጢአት ለማንጻት እንድትሆን ከተቃጠለችው ጊደር አመድ ለርኩሱ ይወስዱለታል፥ በዕቃውም ውስጥ የምንጭ ውኃ ይቀላቀልበታል።

See the chapter Copy




ዘኍል 19:17
11 Cross References  

በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”


በእ​ኔም የሚ​ያ​ምን መጽ​ሐፍ እንደ ተና​ገረ የሕ​ይ​ወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈ​ስ​ሳል።”


አንቺ የገ​ነት ምንጭ፥ የሕ​ይ​ወት ውኃ ጕድ​ጓድ፥ ከሊ​ባ​ኖ​ስም የሚ​ፈ​ስስ ወንዝ ነሽ።


ንጹ​ሕም ሰው የጊ​ደ​ሪ​ቱን አመድ ያከ​ማ​ቻል፤ ከሰ​ፈ​ሩም ውጭ በን​ጹሕ ስፍራ ያኖ​ረ​ዋል፤ ርኵ​ሰት ለሚ​ያ​ነጻ ውኃ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ይጠ​በ​ቃል፤ ይነ​ጹ​በ​ታ​ልና።


የይ​ስ​ሐቅ ሎሌ​ዎ​ችም በጌ​ራራ ሸለቆ ውስጥ ጕድ​ጓድ ቈፈሩ፤ በዚ​ያም ጣፋጭ የውኃ ምንጭ አገኙ።


የላ​ምና የፍ​የል ደም፥ በረ​ከ​ሱ​ትም ላይ የሚ​ረጭ የጊ​ደር አመድ፥ የሚ​ያ​ነ​ጻና የረ​ከ​ሱ​ት​ንም ሥጋ​ቸ​ውን የሚ​ቀ​ድ​ሳ​ቸው ከሆነ፥


ንጹ​ሕም ሰው ሂሶ​ጱን ወስዶ በው​ኃው ውስጥ ያጠ​ል​ቀ​ዋል፤ በቤ​ቱም፥ በዕ​ቃ​ውም ሁሉ፥ በዚ​ያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ አጥ​ን​ቱ​ንም ወይም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን፥ ወይም የሞ​ተ​ውን፥ ወይም መቃ​ብ​ሩን በነ​ካው ላይ ይረ​ጨ​ዋል።


በእ​ሳት ለማ​ለፍ የሚ​ች​ለው ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ ይሆ​ናል፤ ነገር ግን በማ​ን​ጻት ውኃ ደግሞ ይጠ​ራል። በእ​ሳ​ትም ለማ​ለፍ የማ​ይ​ች​ለ​ውን በውኃ ታሳ​ል​ፉ​ታ​ላ​ችሁ።


ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ።


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements