ዘኍል 18:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ይህም ለእናንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ ያቀረቡትን የመጀመሪያ ቍርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ የዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 “እስራኤላውያን ከሚያቀርቡት ስጦታ፣ ከሚወዘወዘው ቍርባን ተለይቶ የሚቀመጠው ስጦታ ሁሉ የአንተ ይሁን። ይህንም ለአንተ፣ ለወንድና ለሴት ልጆችህ መደበኛ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ። ከቤተ ሰዎችህ በሥርዐቱ መሠረት የነጻ ማንኛውም ሰው ከዚሁ መብላት ይችላል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ይህም ደግሞ ለአንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ የሚያቀርቡትን የመወዝወዝ ቁርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 “በተጨማሪም እስራኤላውያን በእኔ ፊት በመወዝወዝ የሚያቀርቡአቸው ልዩ ስጦታዎች ሁሉ የእናንተ ይሆናሉ፤ እነርሱን ለአንተ፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻለሁ፤ ንጹሕ የሆነ ማንኛውም የቤተሰብህ አባል ሊመገባቸው ይችላል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 የተቀደሰ ይሆንልሃል። ይህም ለአንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ ያቀረቡትን የማንሣትና የመወዝወዝ ቍርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘላለም ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። See the chapter |