ዘኍል 17:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ትለመልማለች፤ በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁ የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 እኔ የምመርጠው ሰው በትርም ታቈጠቍጣለች፤ እስራኤላውያን በእናንተ ላይ ነጋ ጠባ የሚያደርጉትንም ማጕረምረም በዚህ እገታለሁ።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ታቈጠቁጣለች፥ በእናንተም ላይ ያጉረመረሙትን የእስራኤልን ልጆች ማጉረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ከዚያም በኋላ እኔ ለክህነት የምመርጠው ሰው በትሩ በማቈጥቈጥ ትለመልማለች፤ በዚህም ዐይነት እነዚህ እስራኤላውያን በየጊዜው በአንተ ላይ ማጒረምረማቸውን እንዲያቆሙ አደርጋለሁ።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ታቈጠቍጣለች፥ በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁን የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ። See the chapter |