Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 16:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ሁላ​ች​ሁም ጥና​ዎ​ቻ​ች​ሁን ውሰዱ፤ ዕጣ​ንም አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ሁለት መቶ አምሳ ጥና​ዎ​ቻ​ች​ሁን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አምጡ፤ አንተ ደግሞ አሮ​ንም ጥና​ዎ​ቻ​ች​ሁን አምጡ” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እያንዳንዱም ሰው ጥናውን ይወስዳል፤ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ዐምሳ ጥናዎች ይሆናሉ፤ በዚያም ላይ ዕጣን ጨምሮ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል፤ አንተና አሮንም ጥናዎቻችሁን እንደዚሁ ታቀርባላችሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሁላችሁም ጥናዎቻችሁን ውሰዱ፥ ዕጣንም አድርጉባቸው፥ እያንዳንዳችሁም ጥናዎቻችሁን ወደ ጌታ ፊት አምጡ፥ ሁለት መቶ ኀምሳ ጥናዎች፤ አንተም እንዲሁም አሮን እያንዳንዳችሁ ጥናዎቻችሁን አምጡ።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እያንዳንዳችሁ ጥናችሁን ይዛችሁ ኑ፤ በውስጡም ዕጣን ጨምሩበት፤ ከሁለት መቶ ኀምሳ ጥናዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ፊት ዕጣናችሁን ታቀርባላችሁ፤ አንተና አሮንም ዕጣናችሁን ታቀርባላችሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ሁላችሁም ጥናዎቻችሁን ውሰዱ፥ ዕጣንም አድርጉባቸው፥ እያንዳንዳችሁም ጥናዎቻችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት አምጡ፥ ሁለት መቶ አምሳ ጥናዎች፤ አንተ ደግሞ አሮንም ጥናዎቻችሁን አምጡ አለው።

See the chapter Copy




ዘኍል 16:17
5 Cross References  

አሁ​ንም ቁሙ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እፋ​ረ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ያደ​ረ​ገ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጽድቅ ሁሉ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


ለመ​ሠ​ዊ​ያው ክዳን ሥራ​ለት፤ መሸ​ፈ​ኛ​ውን፥ ጽዋ​ዎ​ቹን፥ የሥጋ ሜን​ጦ​ዎ​ቹን፥ የእ​ሳት መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አድ​ርግ። ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከናስ አድ​ርግ።


ሙሴም ቆሬን አለው፥ “ማኅ​በ​ር​ህን ለይ፤ ነገ አንተ፥ ማኅ​በ​ር​ህም ሁሉ፥ አሮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዝግ​ጁ​ዎች ሁኑ።


እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጥና​ውን ወሰደ፤ እሳ​ትም አደ​ረ​ገ​በት፤ ዕጣ​ንም ጨመ​ረ​በት፤ ሙሴና አሮ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ቆሙ።


በፊ​ታ​ቸ​ውም ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰባ ሰዎ​ችና የሳ​ፋን ልጅ ያእ​ዛ​ንያ ቆመው ነበር፤ ሰውም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በእጁ ጥና​ውን ይዞ ነበር፥ የዕ​ጣ​ኑም ጢስ ሽታ ይወጣ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements