Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 11:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሕዝ​ቡ​ንም በላ​ቸው፦ ሥጋ ማን ያበ​ላ​ናል? በግ​ብፅ ደኅና ነበ​ረ​ልን እያ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አል​ቅ​ሳ​ች​ኋ​ልና ለነገ ተቀ​ደሱ፤ ሥጋ​ንም ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሥጋን ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ትበ​ሉ​ማ​ላ​ችሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ለሕዝቡ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ነገ ሥጋ ትበላላችሁና ራሳችሁን በመቀደስ ተዘጋጁ። “በግብጽ ተመችቶን ነበር፤ አሁን ግን ሥጋ ማን ይሰጠናል!” ብላችሁ ያለቀሳችሁትን እግዚአብሔር ሰምቷል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሥጋ ይሰጣችኋል፤ እናንተም ትበላላችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሕዝቡንም እንዲህ በላቸው፦ ለነገ ተቀደሱ፥ ሥጋንም ትበላላችሁ ምክንያቱም እንዲህ እያላችሁ ያለቀሳችሁት ለቅሶ ወደ ጌታ ጆሮ ደርሶአልና፦ ‘የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል? በግብጽ ሳለን በዚያ ደኅና ነበርን፤’ ስለዚህ ጌታ ሥጋን ይሰጣችኋል፥ ትበላላችሁም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 አሁንም ለሕዝቡ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ለነገ ራሳችሁን አንጹ፤ የምትበሉትም ሥጋ ይኖራችኋል፤ የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል ብላችሁ ማልቀሳችሁንና የግብጽ ምድር ይሻለን ነበር ማለታችሁን እግዚአብሔር ሰምቶአል፤ እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ሥጋ ይሰጣችኋል፤ እርሱንም ትበላላችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሕዝቡንም በላቸው፦ የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል? በግብፅ ደኅና ነበረልን እያላችሁ ያለቀሳችሁት ወደ እግዚአብሔር ጆሮ ደርሶአልና ለነገ ተቀደሱ፥ ሥጋንም ትበላላችሁ፤ እግዚአብሔርም ሥጋን ይሰጣችኋል፥ ትበሉማላችሁ።

See the chapter Copy




ዘኍል 11:18
16 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ውረድ፤ ዛሬና ነገ ራሳ​ቸ​ውን ያንጹ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ያጥቡ ዘንድ ሕዝ​ቡን እዘ​ዛ​ቸው።


አባ​ቶ​ቻ​ችን ለእ​ርሱ መታ​ዘ​ዝን እንቢ አሉ፤ ከዱ​ትም፤ ልባ​ቸ​ው​ንም ወደ ግብፅ ሀገር መለሱ።


ሕዝ​ቡም በክ​ፋት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በእ​ነ​ርሱ ላይ ነደ​ደች፤ ከሰ​ፈ​ሩም አን​ዱን ወገን በላች።


ሕዝ​ቡም ወደ ቤቴል መጥ​ተው በዚያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እስከ ማታ ድረስ ተቀ​መጡ፤ ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው ጽኑዕ ልቅሶ አለ​ቀሱ።


ተነ​ሣና ሕዝ​ቡን ቀድስ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ‘እስ​ራ​ኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመ​ካ​ከ​ልህ አለ፤ እር​ምም የሆ​ነ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እስ​ክ​ታ​ጠፉ ድረስ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት መቆም አት​ች​ሉም’ ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እስከ ነገ ራሳ​ች​ሁን አንጹ።


ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋጁ፤ ወደ ሴቶ​ቻ​ች​ሁም አት​ቅ​ረቡ” አለ።


ያዕ​ቆ​ብም ለቤተ ሰቡና ከእ​ርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “ከእ​ና​ንተ ጋር ያሉ እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክ​ትን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አስ​ወ​ግዱ፤ ንጹ​ሓ​ንም ሁኑ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም እጠቡ፤


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቀ​ር​ቡት ካህ​ናት ደግሞ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ራሳ​ቸ​ውን ይቀ​ድሱ” አለው።


አንድ ቀን፥ ወይም ሁለት ቀን፥ ወይም አም​ስት ቀን፥ ወይም ዐሥር ቀን ወይም ሃያ ቀን አት​በ​ሉም፤


ቢጠ​ብ​ቃ​ትም፥ ባይ​ተ​ዋ​ትም፤ በጕ​ሮ​ሮ​ውም መካ​ከል ቢይ​ዛት፥ መብሉ በአ​ን​ጀቱ ውስጥ ይገ​ላ​በ​ጣል፤


“ሆዱን ቢያ​ጠ​ግብ፥ የመ​ዓት መቅ​ሠ​ፍት ይጨ​መ​ር​በ​ታል፤ የሕ​ማ​ሙም ሥቃይ ይጸ​ና​በ​ታል።


ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​በ​ትን ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁን ሰም​ቶ​አ​ልና በመሸ ጊዜ ትበሉ ዘንድ ሥጋን፥ በማ​ለ​ዳም ትጠ​ግቡ ዘንድ እን​ጀ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እኛም ምን​ድን ነን? ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ነው እንጂ በእኛ ላይ አይ​ደ​ለም” አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements