Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 1:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ከዮ​ሴፍ ልጆች፥ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከዛብሎን ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 “የዛብሎን ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 የዛብሎን ልጆች፥ በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 የዛብሎን ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥

See the chapter Copy




ዘኍል 1:30
7 Cross References  

“ዛብ​ሎን ጫማ​ውን አዝቦ ይኖ​ራል፤ እር​ሱም እንደ መር​ከ​ቦች ወደብ ይሆ​ናል፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ሲዶና ይሰ​ፋል።


የዛ​ብ​ሎ​ንም ልጆች፤ ሳሬድ፥ አሎን፥ አሌል።


ልያም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካም ስጦ​ታን ሰጠኝ፤ እን​ግ​ዲ​ህስ ከዛሬ ጀምሮ ባሌ ይወ​ደ​ድ​ኛል ስድ​ስት ልጆ​ችን ወል​ጄ​ለ​ታ​ለ​ሁና” አለች፤ ስሙ​ንም ዛብ​ሎን ብላ ጠራ​ችው።


ከዛ​ብ​ሎን ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።


ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ የተ​ቈ​ጠ​ሩት አርባ ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements