Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 7:73 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

73 ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በረ​ኞ​ቹና መዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከሕ​ዝ​ቡም ዐያ​ሌ​ዎቹ፥ ናታ​ኒ​ምም፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

73 ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ። ሰባተኛው ወር በደረሰና እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው በተቀመጡ ጊዜ፣

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

73 ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎቹ፥ መዘምራኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንድ ሰዎች የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ በአጠቃላይ እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው ሰፈሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

73 ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ በረኞቹና መዘምራኑም ከሕዝቡም አያሌዎቹ፥ ናታኒምም፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።

See the chapter Copy




ነህምያ 7:73
7 Cross References  

ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከሕ​ዝ​ቡም አያ​ሌ​ዎች፥ መዘ​ም​ራ​ኑና በረ​ኞ​ቹም፥ ናታ​ኒ​ምም በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።


ገብ​ተ​ውም በከ​ተ​ማው በር ጮኹ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፥ “ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር ገባን፤ እነ​ሆም፥ ፈረ​ሶ​ችና አህ​ዮች ታስ​ረው፥ ድን​ኳ​ኖ​ችም ተተ​ክ​ለው ነበር እንጂ ያገ​ኘ​ነው አል​ነ​በ​ረም፤ የሰ​ውም ድምፅ አል​ነ​በ​ረም።”


በእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞ​ችና በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸው መጀ​መ​ሪያ የተ​ቀ​መጡ ካህ​ናት፥ ሌዋ​ው​ያ​ንም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ነበሩ።


ሰባ​ተ​ኛ​ውም ወር በደ​ረሰ ጊዜ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ሳሉ፥ ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ።


የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ የሰ​ጡት ሃያ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪ​ክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባ​ትም የካ​ህ​ናት ልብስ ነበረ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​ቀ​መ​ጡት የሀ​ገሩ አለ​ቆች እነ​ዚህ ናችው፤ እስ​ራ​ኤል ግን ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ናታ​ኒ​ምም፥ የሰ​ሎ​ሞ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በየ​ር​ስ​ታ​ቸ​ውና በየ​ከ​ተ​ማ​ቸው በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ተቀ​መጡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements